በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የእሣት ማጥፊያ መሣሪያዎች ፍተሻና ሙሌት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ሙሲፋ/Re-23/2018
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የእሣት ማጥፊያ መሣሪያዎች ፍተሻና ሙሌት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የ2019 ዓ/ም የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የታክስ ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና ጊዜው ያላለፈበት የታክስ ክሊራንስ ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ገርጂ የቀድሞው ኢምፔሪያል ህንፃ ከሚገኘው የፋብሪካው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዕለቱ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
