Tender Detail

Tender Details

  • Company Worabe Comprehensive Specialized Hospital (የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)
  • Address ወራቤ : ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0463299263
  • Websitehttps://www.worabecsh.org/
  • Deadline24 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400(አራት መቶ ብር)
  • Bid Security20,000 በባንክ በተመሰከረ C.P.O /ሲፒኦ/
  • opening dateበዕለቱ ከሰዓት በኋላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። የመክፈቻውም ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  • Categories Chemicals And Reagents , Pharmaceutical Products , Laboratory Equipment And Chemicals

የወራቤ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት ለስራ ክፍሎች የሚያገለግሉ፡- ሎት 1- መድኃኒቶችን ሎት 2- የላብራቶሪ ሪኤጀንቶችን ለመግዛት ይፈልጋል።

Worabe Comprehensive Specialized Hospital (የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)


የጨረታ ማስታወቂያ

የወራቤ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት ለስራ ክፍሎች የሚያገለግሉ፡-

ሎት 1- መድኃኒቶችን

ሎት 2- የላብራቶሪ ሪኤጀንቶችን ለመግዛት ይፈልጋል።

ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለዕቃዎች የሚገልፅ ሰነድ (ዶክመንት) በወራቤ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።

  1. ተጫራቾች ተፈላጊ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚያስችላቸውን የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) እና የታደሰ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  2. የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 20,000 በባንክ በተመሰከረ C.P.O /ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በተለያዩ ፖስታዎች ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30-6፡30 ሰዓት፣ ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  5. ጨረታው በ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከሰዓት በኋላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። የመክፈቻውም ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  6. ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0463299263 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የወራቤ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

✨ messages.ai_summary
Worabe Comprehensive Specialized Hospital seeks suppliers for Lot 1: pharmaceuticals and Lot 2: laboratory reagents. Bidders must provide a renewed business license, TIN, and renewed Food and Drug Authority certificate, and be registered on the Ministry of Finance and Economic Development suppliers list.
Save Tender