በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በትምህርት ጽ/ቤት አማካይነት ለሚያሰራው የደሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አራት ክፍል (አንድ ብሎክ) ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
መለያቁጥር GGWW/0003/2019
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በትምህርት ጽ/ቤት አማካይነት ለሚያሰራው የደሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አራት ክፍል (አንድ ብሎክ) ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።ስለሆነም ተጫራቾች
- የዘመኑን ንግድፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበርተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/BC ደረጃ 6 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮች
- ከገቢዎች መስሪያ ቤት የኦዲት ክሊራንስ ማምጣት የሚችሉ
- ተወዳዳሪዎች የቫት 7.5%ተቀናሽ ለማድረግ ፍቃደኛ መሆን አለባቸው
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ የድርጅቱ ባለቤት መሆን አለባቸው እንዲሁም በውክልና ሰነዱን መውሰድና መወዳደር አይቻልም።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8:00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀልአምባ ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ 200000 ሁለት መቶ ሺህ ብር በገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየትለ /ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15( አስራ አምስት ) ተከታታይ ቀናት መሀልአምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሰነድ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ይታሸጋል ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መስሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ:-
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም።
- ተጫራቾች ተጫርተው ከሻነፉ በኋላ አገልግሎታቸው ጥራት ያለውና ቀልጣፋ ካልሆነ የውል ጊዜን የምናቋርጥ መሆኑን እንገልፃለን።
- ጨረታ የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
- ተወዳዳሪዎች ከአሸነፉ በኋላ ቅድመ ክፍያ ሳይጠይቁ ስራውን መስራት የሚችሉ መሆን አለባቸው ።
- በወረዳው ውስጥ አንድም ፕሮጅክት የያዘ አካል መወዳደር አይችልም።
ለበለጠ መረጃ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ቢሮ ስልክ ቁጥር 0113360631/146 ይደውሉ
✨ messages.ai_summary
Construction of four classrooms (one block) for Desa Secondary School, procured by the Finance Office of Gedebano Gutazer Welene Woreda, Central Ethiopia Region, through the Education Office. Open to contractors with GC/BC Grade 6 or above holding a valid trade license, VAT and TIN registration, and an audit clearance.
