የመኪና መለዋወጫ፣ ጎማና ባትሪ፣ ዘይትና ቅባት እና የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ (4 ሎቶች) - በሰ/ጎንደር ዞን የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ላሉ የመንግስት ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል ሎት አንድ የመኪና መለዋወጫ ሎት ሁለት የመኪና ጎማ ፤ ባትሪ ሎት ሶስት ሶስት የመኪና ዘይትና ቅባት ሎት አራት የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል ።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ።
- የታደሰ የንግድ ምዝገባ ወረቀት ያላቸው
- ከታክስ ባለስልጣን ገቢዎች ጽ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
- ግዢ ከ500, 000/አምስት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተቁ ከ1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎች ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ መሂ/1 ማስያዝ የሚችል እና አሸናፊ ከሆነ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ መ/ሂ/1 ማስያዝ የሚችል ።
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ውል የሚወስደው በበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት እና ፍትህ ጽ/ቤት ይሆናል ወይም በገንዘብ ጽቤት ብቻ ይሆናል፡፡ አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በጠቅላላ ድምር መሆኑን የተረዳ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከ29/01/2019 ዓ/ም እስከ 08/02/2019 ዓ/ም በበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ 500/አምስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11፡30 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ትችላላቹሁ።
- የጨረታ ሳጥኑን በ09/2/2019 ዓ/ም 9፡00 ታሽጎ ከቀኑ 9፡30 ህጋዊ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት እና የሚታሸግበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ካላንደር ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን 9፡00 ታሽጎ ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ህጋዊ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ ይከፈታል፡
- የጨረታ አሸናፊው ሎት አንድን ጎንደር ከተማ ማቅረብ የሚችል እና በተጠየቀ በአምስት ተከታታይ ቀናት ኦርጅናል እቃ ማቅረብ የሚችል። ሌሎቹን ሎቶችን ግን በየዳ ወረዳ ድል-ይብዛ ከተማ በአራቱ ንብረት መጋዘን ማቅረብ የሚችል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በተሰጠው ዝርዝር መሰረት ስርዝ ድልዝ በሌለው መሙላት የሚችል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በተጫራቾች መመሪያ ወይም በስልክ ቁጥር 0918352228 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Supply of vehicle spare parts, tires, batteries, oil and lubricants, and transportation services for government vehicles in Beyeda Woreda, in four lots. Open to bidders with a valid trade license, TIN, business registration, tax clearance, and VAT registration certificate if the purchase exceeds 500,000 birr.
