በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የሚኪሊላንድ ጤናጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የሚኪሊላንድ ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የሚኪሊላንድ ጤናጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎትአንድ፡- የፅዳት ዕቃዎች ጨረታ ማስከበሪያ cpo (5,000 ብር)
- ሎትሁለት፡- የደንብ ልብስ ጨረታ ማስከበሪያ cpo (18,000ብር)
- ሎትሶስት፡- የተለያዩ ህትመቶች ጨረታ ማስከበሪያ cpo (10,000ብር)
- ሎትአራት፡- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ጨረታ ማስከበሪያ cpo(20,000ብር)
- ሎትአምስት፡- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ጨረታ ማስከበሪያ cpo(45,000ብር)
- ሎትስድስት፡- ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ጨረታ ማስከበሪያ CPo(1,500)
- ሎትሰባት፡- ኤሌክተሮኒክስ ጥገና ጨረታ ማስከበሪያ cpo (5000 ብር)
- ሎትስምንት፡- የህንጻ እድሳት እና ጥገና ጨረታ ማስከበሪያ cpo (40,000ብር)
- ሎትዘጠኝ፡- የደንብ ልብስ ስፌት ጨረታ ማስከበሪያ cpo (2,000ብር)
- ሎት አስር፡- መድኃኒት እና ሪኤጀንቶች ጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (20 , 000 ብር)
- ሎት አስራ አንድ፡- የትራንስፖርት አገልግሎት ጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (5,000 ብር)
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃዳቸውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬትና የዘመኑን ግብር የከፈሉትን ማስረጃ እንዲሁም በገንዘብ ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር /400/አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጤና ጣቢያው ግዥ ክፍል 3ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 52 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ላሸነፈበት ዕቃ በእያንዳንዱ ሎት የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ለየብቻ ኦርጅናሉን ከአንድ ኮፒ ጋር እስከ ጨረታው 10ኛ እና የመጨረሻ እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚያበቃው ጋዜጣው አየር ላይ በዋለበት በአስርኛው ቀን 11፡30 ያበቃል
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊወ ኪሎቻቸው በሚገኙበት በ3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት በጤና ጣቢያው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሳንፕል ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የአቅራቢነት ሊስት የኦን ላይ የተመዘገበ መሆን አለበት ፡፡
- በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅታቹ ለምትመጡ ካደራጃችሁ ወረዳ የምታመረቱበት ምርት ብቻ የውል ማስከበሪያ እና የጨረታ ውል ማስከበሪያ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸውል ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠየበቀ ነው
- ማንኛውም ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ከጨረታው ውጭ ያደርጋል ፡፡
ለበለጠመረጃ፡- በስልክ ቁጥር/0112731970
አድራሻ፡- አስኮ ብርጭቆ ወይም ሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም መሀል አደባባይ አካባቢ በስተቀኝ በኩል ሚኪሊላንድ ጤና ጣቢያ ግዥ ክፍል 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 52
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የሚኪሊላንድ ጤና ጣቢያ
✨ messages.ai_summary
Mikililand Health Station invites bids for various office supplies and related goods under an open tender, divided into 11 lots covering cleaning materials, uniforms, printing, office supplies, equipment, electronics repair, building renovation, pharmaceuticals and transport services. Bidders must submit a valid business license, VAT registration, tax payment proof, and supplier registration certificate.
