የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ የሚገኙ ከዚህ በታች የተገለጹትን ያገለገሉ ንረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ የሚገኙ ከዚህ በታች የተገለጹትን ያገለገሉ ንረቶችን:-
| የሎት ቁጥር | የንብረቶቹ ዓይነት |
| ሎት-1 | የተለያዩ ያገለገሉ ቀላል ተሽከርካሪዎች |
| ሎት-2 | የተለያዩ ያገለገሉ ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ የከባድ ተሽከርካሪ ተሳቢዎችና አውቶቢሶች |
| ሎት-3 | የተለያዩ ያገለገሉ የእርሻ መሣሪያዎችን፣ ዶዘሮችና ሌሎችን |
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች:-
- ሀ) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት አዲስ አበባ ቃሊቲ መጨረሻ ባቡር ፌርማታ ጋር ሲደርሱ አዋሽ ባንክ ካለበት ህንጻ በስተጀርባ በኮርፖሬሽኑ የግብርና ምርት ማስፋፊያ አቅርቦ ዘርፍ ህንጻ 3ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ፋይናንስ ገንዘብ ያዥ(ካሸር) ቢሮ እንዲሁም በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማለትም(በአሰላ፣ በአርዳይታ፣ በኮፈሌና በሀዋሳ) በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ለ) የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚከሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ ጨረታውም በ10ኛው የሥራ ቀን ማለትም በ (12/02/2019 ዓ.ም) ከቀኑ 10:00 ሰዓት ተዘግቶ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰነዶች ተሰብስበው ከመጡ በኋላ በ 19/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ሐ) ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም:-
- ሎት 1:- ላገለገሉ አነስተኛ ተሽከርካሪዎች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ንብረት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፤
- ሎት 2:- ለተለያዩ ያገለገሉ ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ የከባድ ተሽከርካሪ ተሳቢዎችና አውቶቢሶች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ንብረት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፤
- ሎት 3:- ለተለያዩ ያገለገሉ የእርሻና ኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እና ሌሎች ንብረቶች ለእያንዳንዳቸው ለሚወዳደሩበት ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መ) ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ንብረት የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (ተ.እ.ታ) በፊት በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ በዝርዝር በማመልከት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ሠ) ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ:- አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ ከፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበር ጀርባ ወይም EBG /VOLVO ቀጥሎ ወደ ዉስጥ በሚያስገባው መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር:- 0920577343 ፣ 0911166473 ፣ 0949632090
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Agricultural Works Corporation invites bids for the open tender sale of used vehicles, machinery and equipment in three lots: light vehicles; heavy vehicles, trailers and buses; and agricultural machinery, dozers and other items. Bidders must meet the stated requirements.
