በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መለቅ የስልጤ የገበሬዎች ህ/ስ/ዩኒየን በ2019 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው የጫጩት መፈልፈያ ማስፋፊያ ግንባታ ለማስገንባት በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Melik Silte's Farmers' Cooperative Union
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መለቅ የስልጤ የገበሬዎች ህ/ስ/ዩኒየን በ2019 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው የጫጩት መፈልፈያ ማስፋፊያ ግንባታ ለማስገንባት በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ደረጃቸው B.C-4/G.C-5 እና ከዛ በላይ የሆኑ፤
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርብ፤
- የታደሰ የንግድ ፈቃድና የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ሚኒስተር የዘመኑን የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ፤
- የጨረታ ዋስትና 150,000 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችሉ፤
- የመስራት አቅም እንዳላቸው የሚገልፅ የወቅቱን የባንክ እስቴትመንት እና የስራ ልምድ ብቃት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የኦዲት ሪፖርት እና የድርጅቱን አወቃቀርና ከዚህ በፊት የሰሯቸውን ስራዎች የሚገልፅ የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮች ሰነዱን ከመሊቅ የስልጤ የገበሬዎች ህ/ስ/ዩኒየን ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር በመቅረብ ለሰነድ የማይመለስ ብር 1000/አንድ ሺህ ብር/ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሽያል ዶክመንቱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናል እና 2ኮፒ ለየብቻ፣ ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ መሊቅ የስልጤ የገበሬዎች ህ/ስ/ዩኒየን ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፦
- ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንስ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡
- የተወዳዳሪ ተቋራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀኑን አይለውጠውም፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፦ ስልክ ቁጥር 0920999940 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
በማዕ/ኢ/ክ/መ መሊቅ የስልጤ የገበሬዎች ህ/ስ/ዩኒየን ፋይናንስ ክፍል
✨ messages.ai_summary
Melik Silte Farmers' Cooperative Union seeks licensed contractors for the construction of a chick hatchery expansion. Eligible bidders must hold grade B.C-4/G.C-5 or above, provide tax and VAT registration, renewed trade and work licenses, and proof of capacity and experience.
