የቢሮ እድሳት ሥራ - የሰሜን ቤንች ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት (ቤንች ሸኮ ዞን)
በደ/ም/ኢት/ህ/ክ/መንግስት በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
የቢሮ እድሳት ሥራ የጨረታ ማስታወቂያ
በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ፋይናንስ/ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት የሰሜን ቤንች ወረዳ በካፒታል በጀት (የሰ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት የሚገለገልበትን ቢሮ) ማሳደስ ስለተፈለገ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች ለማቅረብ የሚያስችል በዘርፉ የታደሰ የ2019 ዓ.ም የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው መሆን አለበት፡፡
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
- ቲን ነምበር እና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት vat) ተመዝጋቢ የሆነበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ CPO 20,000(ሀያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የተጫራቾች ወይም የተወካይ ፊርማ እና እንዲሁም የድርጅት ማህተም መኖር አለበት፡፡
- ተጫራቾች እያንዳንዱ ፖስታ ላይ የሚወዳደሩበትን የሥራ ቦታ የድርጅት አድራሻ የተጫራች ወይም የተወካዩን ስልክ ቁጥር በመግለጽ መፃፍ አለበት ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ተወዳድራችሁ ካለፋችሁ የመጀመሪያ ዙር ከፍያ የሚጠይቁ ከሆነ ለከፍያው ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ18 የመንግሥት የሥራ ቀናት ውስጥ በሰ/ቤ/ወ/ገ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት የጨረታ ሰነድ መግዣ ክፍያዉን የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሕጋዊ ደረሰኝ በመያዝ በሰ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-4 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ (1)አንድ ኦርጅናል እና (2) ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያዩ 3 ፖስታዎች ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱ ላይ ሕጋዊ ማህተማቸውን እና ፊርማቸውን ማስፈር ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተጨማሪ በጨረታ ዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- በግንባታ ዘርፍ ደረጃ-9 እና ከዚያ በላይ ያለው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መልካም የሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችል
- ጨረታ የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ18ት የመንግሥት የሥራ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ19ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ታሽጎ ልክ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ባይገኙም አንገደድም ፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0946521985 /0935170895 ይደውሉ፡፡
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/ መንግሥት በቤንች ሸኮ ዞን
የሰሜን ቤንች ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Renovation of the North Bench Woreda Finance Office building in Bench Sheko Zone. Open to licensed building contractors with grade 9 or above, renewed 2019 license, tax clearance, VAT registration, and CPO. Bidders must submit one original and two copies in three sealed envelopes.
