Tender Detail

Tender Details

  • Company BUNNA INSURANCE S.C (ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ)
  • Address ሳር ቤት ወይም አፍሪካ ህብረት ጀርባ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-126-31-03
  • Websitehttps://www.bunnainsurance.com/
  • Deadline19 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineREPORTOR
  • Bid Document Price300(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Security100,000 (CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና)
  • opening dateጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
  • Categories Pumps, Motors And Compressors , Cargo Vehicle , Automotive Materials

ቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በዝርዝር የተገለፁትን ተሽከርካሪዎች እና ተዛማጅ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

BUNNA INSURANCE S.C (ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ)


ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ

Bunna Insurance S.C

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በዝርዝር የተገለፁትን ተሽከርካሪዎች እና ተዛማጅ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል::

ተ.ቁየእቃው ዝርዝርየሎት ብዛትየጨረታ ማስከበሪያ መጠን
1Single Cab Pickup ,Double Cab Pickup, light duty Electric car, ISUZU 5 Ton Rollback Wrecker Truck & Submersible Water PumpLot (ሎት) 3100,000

በጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች፡-

  1. ከላይ በሎት ሶስት የተገለፁትን የግዥ ዝርዝሮች ውስጥ በተናጠል ወይም በጥቅል(በሁሉም) የእቃ ዓይነት መወዳደር ይችላሉ::
  2. በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የታደሰ የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  3. በሎቱ የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን በኩባንያችን ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብቻ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: ከተጠቀሰው መጠን በታች ወይም ከተገለፀው አይነት የተለየ ያስያዘ ተጫራች ከጨረታ ውጭ የሚደረግ ይሆናል::
  4. ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ከአፍሪካ ሕብረት ጀርባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የቡና ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋናው መ/ቤት የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ሁለተኛ ፎቅ ፋይናንስ መምሪያ ክፍያ በመፈፀም የጨረታ ሰነዱን ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል (ምድር ቤት) በመምጣት መውሰድ ይችላሉ::
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  6. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በኩባንያው ዋና መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ (ምድር ቤት) ይከፈታል::
  7. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114-705908 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::
  8. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ፡-
ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት
ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል
የስልክ ቁጥር፡- 0114-705908 /011-126 — 31 - 03
አዲስ አበባ

✨ messages.ai_summary
Bunna Insurance S.C invites bidders to supply vehicles and related items: single cab pickup, double cab pickup, light duty electric car, ISUZU 5-ton rollback wrecker truck, and submersible water pump, as one lot. Bidders may bid separately or as a package. Valid trade license, registration, tax and VAT certificates required.
Save Tender