Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፈዴሬሽን ኃላ/የተ/ አሰላ ብቅል ፋብሪካ
  • Address አዲስ አበባ ከተማ ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወስደው መንገድ ላይ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፈዴሬሽን ሕንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ወይም አሰላ- ቁሉምሳ : ኢትዮጵያ, Phone: 09-65-65-04-81
  • Website
  • Deadline23 Oct 2026, 10:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid SecurityLOT:1 ብር 50,000.00፤ LOT:2 ብር 50,000.00፤ LOT:3 ብር 30,000.00፤ LOT:4 ብር 25,000.00 (CPO)
  • opening dateበ22ኛው ቀን LOT:1 እና LOT:2 ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ላይ፤ LOT:3 እና LOT:4 ከረፋዱ 6:00 ሰዓት ላይ
  • Categories Hand Tools And Workshop Equipment , Mechanical Work and Materials , Electrical Materials

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን – አሰላ ብቅል ፋብሪካ የWorkshop, Electrical, Bearing/Seal/V-Belt እና Mechanical & Electrical Tools ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ተጫራቾችን ይጋብዛል።

በኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፈዴሬሽን ኃላ/የተ/ አሰላ ብቅል ፋብሪካ


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ:-

LOT: 1. Workshop Materials - NCB/OACFLTD/AMF/01/2019

LOT: 2. Electrical Materials :-NCB/OACFLTD/AMF/02/2019

LOT: 3. Bearing, Mechanical Seal and Oil Seal and V-Belt:- NCB/OACFLTD/AMF/03/2019

LOT: 4.Mechanical and Electrical Tools:- NCB/OACFLTD/AMF/04/2019

ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በመጋበዝ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው::

  1. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
  2. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በፋብሪካችን አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000257808697 ወይም በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1000043405229 በመክፈል/ገቢ በማድረግ::
    • ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት 2:00-6:00 ከሰዓት በኃላ 7:00-10:00 ሰዓት ድረስ ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወስደው መንገድ ላይ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ወይም አሰላ-ቆሉምሳ ከሚገኘው ፋብሪካችን ቢሮ ቁጥር 003 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
  3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በፖስታ በማሸግ አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና መ/ቤት በኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከታች ከተጠቀሰው የመዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለLOT:1 ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ፤ለLOT:2 ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)፤ለLOT:3 ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) እና ለLOT:4 ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ለየብቻ በማስያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  5. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን:-ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን LOT:1 እና LOT:2 ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ላይ፤ LOT:3 እና LOT:4 ከጠዋቱ 5:30 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 6:00 ሰዓት ላይ ለመገኘት በሚሹ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና መ/ቤት የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ ሰባተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል::
  6. ፋብሪካው በዚህ ጨረታ ሰነድ ከተገለጸው ብዛት 20% (ሃያ በመቶ) በመቀነስ ወይም 30% (ሰላሳ በመቶ) በመጨመር በተመሳሳይ ዋጋ መግዛት ይችላል::
  7. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ተጫራቾች በጨረታ ማስታወቂያና በተጫራቾች መመሪያ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነጥብ ካለና ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር:- 09 65 65 04 81 / 09 65 65 02 85 በሥራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ

✨ messages.ai_summary
Oromia Agricultural Cooperatives Federation's Asella Blanket Factory invites bids for four lots: workshop materials, electrical materials, bearings/mechanical seals/oil seals/V-belts, and mechanical and electrical tools. Bidders must have a renewed business license, be registered as suppliers, have a TIN, and be VAT-registered.
Save Tender