Tender Detail

Tender Details

  • Company በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
  • Address ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-131-01-08
  • Website
  • Deadline23 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበ22ኛው ቀን ጠዋት 4:30 ሰዓት (22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት)
  • Categories Agriculture And Farming , Agricultural

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጌዴኦ ዞን ግብርና መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙት ለቡሌ እና ለራጴ ወረዳ አሲዳማ አፈርን ለማሻሻል አገልግሎት የሚውል የአፈር ኖራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት


የአፈር የኖራ ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጌዴኦ ዞን ግብርና መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙት ለቡሌ እና ለራጴ ወረዳ አሲዳማ አፈርን ለማሻሻል አገልግሎት የሚውል የአፈር ኖራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፣

  • በበጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
  • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
  • የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
  • በግብርና ሚኒስቴር የጥራት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣

ከላይ በዝርዝር የተቀመጡ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፤ ቫትን ያላከተተ ከሆነ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ሲፒኦ፣ ወይም በባንክ ዋስትና ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጅናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኃላ ከሲፒኦ ጋር በአንድ ትልቅ ፖስታ በስም በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
  • ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ /በፍሉድ/ የተስተካከለ በሚታይ መልኩ በድጋሚ ተጽፎ በተጫራች ወይም በህጋዊ ተወካዩ መፈረም አለበት፤
  • በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፤
  • ጨረታዉ የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት ከተከታታይ በሚቆጠር 21 ቀናት በኋላ በ22ኛው ቀን ጠዋት የጨረታው ሳጥን በ4:00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች በዕለቱ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ሠዓት ባለው ጊዜ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • የጨረታው ሳጥን የሚገኘው በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ቅጥር ግቢ ግዥና ንብ/አስ/ዋና ሥራ ሂደት ነው፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉትን ኖራ ጌዴኦ ዞን ቡሌ ከተማ እና ራጴ ወረዳ ሃሮ ወላቦ ቀበሌ ድረስ የማጓጓዣ ፣ የማስጫኛ እና የአውራጅ ወጪ ችለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር፡- 046-131-01-08 መደወል ይችላሉ፡፡

በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ዋና ሥራ ሂደት
/ዲላ/

✨ messages.ai_summary
Gedeo Zone Agriculture Department seeks bidders to supply soil lime to improve acidic soil in Bule and Rape woredas. Bidders must hold a renewed business license, VAT and supplier registration, TIN, and an agriculture ministry quality certificate, and deliver the lime to the specified sites.
Save Tender