Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
  • Address አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-56-98-69
  • Websitehttps://press.et/
  • Deadline19 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 260,000 (CPO/ቢድቦንድ)
  • opening dateበዕለቱ ከረፋዱ 4:30 ሰዓት (10:30 AM) ይከፈታል
  • Categories Ict And Telecom Service , NonConsultancyServices

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጸውን የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)


የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ለሦስተኛ ጊዜ በድጋሚ የወጣ

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡-ኢፕድ 009/2019

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጸውን የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።በዚህም መሰረት፡-

በውል ለአንድ ዓመት የሚፈጸም የጥሪ ማዕከል የአገልግሎት ግዥ

ስለሆነም፡- ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።

  1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ፣ ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
  2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በአቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር ማስያዣ ብር 260,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ቢድቦንድ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ ዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ አለባቸው።
  4. ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምሪያ ከረፋዱ 4:00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4:30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ይከፈታል ።ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 011 1 56 98 69

ኢሜይል procurement@press.et

አድራሻ፡- አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊትለፊት

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Press Agency seeks a one-year call center service contract via open tender. Bidders must have a valid business license, commercial registration, taxpayer and VAT certificates, tax clearance, and be registered as government suppliers.
Save Tender