የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ በውል ለአንድ ዓመት መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር:-ኢፕድ 008/2019
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ በውል ለአንድ ዓመት መግዛት ይፈልጋል፡፡በዚህም መሰረት፡-
- ሎት1 በውል የሚፈጸም የአማካሪ አገልግሎት ግዥ
- ሎት2 የፋይናንስ ሰነድ ማስተማመኛ ሽፋን
- ሎት3 በውል የሚፈጸሙ የካኑት ዕቃዎች ኪራይ አገልግሎት ግዥ
ስለዚህም፡- ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በሙያ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ፣በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ04 በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማሸግ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በአቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር
- ሎት 1 ብር 20,000.00
- ሎት 2 ብር 50,000.00
- ሎት 3 ብር 50,000.00
- ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምሪያ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4:30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አሮጌው ፎቅ መሰረዩ ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ምድር ላይ ይከፈታል፡፡ሆኖም ግን የመክፈቻው ቀን በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 011 1 56 98 69
ኢሜይል procurement@press.et
አድራሻ አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊትለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Press Enterprise seeks suppliers for a one-year contract via open tender, covering three lots: consultancy services, financial document insurance coverage, and rental of canut items. Bidders must hold a valid business license, tax registration, VAT certificate, tax clearance, and be registered as government suppliers.
