በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በግልፅና በሐራጅ ጨረታ የኮንትሮባንድ እቃዎችን (ጫማና አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ ሞባይልና ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ የሳሙና ፋብሪካ ማሽነሪና ሌሎች) በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈዉ የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 27/01/2019 እና በ30/01/2019 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላከሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
| ተ.ቁ | የጨረታ ቦታ | የጨረታው ዓይነት | በጨረታ የቀረቡ እቃዎች | የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ | የጨረታዉ የመዝጊያ እና የመከፈቻ ቀንና ሰዓት |
| 1. | ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት | ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ | ጫማዎች አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ -ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ፣ የስፖርት እቃዎች የእጅ ሰዓት ኮስሞቲክስ፣ መነፅር፣ ጌጣ ጌጦች የሳሙና ፋብሪካ አካል ማሽነሪ እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች፡፡ | ለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ 27/01/2019 እና በ30/01/2019 እስከ ጠዋቱ 3፡45 | ለግልጽ ጨረታ 27/01/2019 እና በ30/01/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ 27/01/2019 እና በ30/01/2019 ዓ/ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡ |
የጨረታ መስፈርቶች፡-
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት ዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራንስ (Clearancs) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታከሲ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸዉ የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 27/01/2019 እና በ30/01/2019 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላከሎት ማድረግ ይችላሉ።
- ግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተዉ በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።
- የጨረታዉ መክፈቻ ቦታ- በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
- ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታዉ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸዉ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታዉ ዉጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዘን ማውጣት ይኖርበታል፡፡
- ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
The Awash Customs Office seeks to sell confiscated contraband goods—shoes, clothing, vehicle spare parts, mobile/electronics, cosmetics, food items, sports goods, watches, eyeglasses, jewelry, soap factory machinery, and more—via open and auction bidding at Kaliti Customs Office. Bidders need a renewed business license, VAT registration, tax clearance, and recent VAT activity certificate.
