ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ - የወተር ትሪትመንት፣ የስኳር ምርት አገልግሎት እና የላብራቶሪ ኬሚካል፣ የስኳር ፋብሪካ ፓምፕ እና የፓምፕ መለዋወጫ ዕቃዎች እና የስኳር ፋብሪካ መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: ጣበስፋ/አግ/ብግጨ/03/2019
በሎት-1 የወተር ትሪትመንት፣ የስኳር ምርት አገልግሎት እና የላብራቶሪ ኬሚካል
በሎት-2 የስኳር ፋብሪካ ፓምፕ እና የፓምፕ መለዋወጫ ዕቃዎች
በሎት-3 የስኳር ፋብሪካ መለዋወጫ ዕቃዎች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ሕጋዊ የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ/ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ አግባብነት ያለው አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
- ጨረታው መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ ይዘጋል:: ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢ.ንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተራ ቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል:: ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል::
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000057735167 በመክፈልና የባንክ አድቫይስ በማቅረብ በተራ ቁ. 4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ::
- የጨረታው ማስረከቢያና መክፈቻ አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው::
አዲስ አበባ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ተዘንአ ሆስፒታል አካባቢ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሕንፃ
ብሎክ A ቢሮ ቁጥር B008
ስልክ ቁጥር 011 5-586725
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ - ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ የጠቅላላ ዋጋውን 2% ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው::
- የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው::
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011558-67-25 ደውሎ መጠየቅ ይችላል::
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
✨ messages.ai_summary
Tana Beles Sugar Factory seeks national open tender bids for water treatment, sugar production services and lab chemicals (Lot 1), sugar factory pumps and pump spare parts (Lot 2), and sugar factory spare parts (Lot 3). Bidders must submit renewed business license, tax clearance, VAT registration, and supplier list certificate.
