Tender Detail

Tender Details

  • Company የአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል
  • Address አራት ኪሎ ስፖርት፣ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ቢሮ ቁጥር 7 ከስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 1 261365
  • Website
  • Deadline05 Oct 2026, 5:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500 ብር (አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ሲፒኦ/CPO በባንክ የተረጋገጠ
  • opening dateበማግስቱ የሥራ ቀን ከሆነ ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት
  • Categories Food And Beverage , Food Items And Drinks

ለመጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የምግብ ግብዓት በሥራ መስክ፣ የዘመኑን ግብር፤ ለመከፈላቸውን ሕጋዊ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

የአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል


የምግብ ግብዓቶች ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2019 ዓ.ም

በአራት ኪሎ ስፖርት፣ ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል

  1. የምግብ ግብዓቶች ለአንድ ዓመት በአቅራቢነት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የተጫራቶች መመሪያ

በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቶች

  1. ለመጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የምግብ ግብዓት በሥራ መስክ፣ የዘመኑን ግብር፤ ለመከፈላቸውን ሕጋዊ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. በመንግሥት የግዥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል Tin No. ያላቸውና በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉበትና የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  4. የዋጋ ማቅረቢያ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እንዲኖር አይፈለግም። ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታው ውጪ ይሆናል።
  5. ተጫራቾች በሙሉም ሆነ በከፈል ጨረታውን ተወዳድረው ካሸነፉና ከተዋዋሉ በኋላ ያሸነፉበትን ዕቃ በተሰጠው ለአንድ ዓመት ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ ካልሆነ በውሉ መሠረት በሕግ ይጠየቃል። ለምግብ ግብዓት ባሸነፈው የዋጋ ጭማሪ ካለ ለሦስት ወር ከአቀረቡ በኋላ ከሀገሪቱ ገበያ ዋጋ ጋር ግምት ውስጥ ገብቶ ተነፃፅሮ ዋጋ ይሻሻላል።
  6. ተጫራቶች መ/ቤቱ ያዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የምግብ ዝርዝር የያዘው የአንዱ ዋጋ ከነቫት መሙላት ይኖርባቸዋል። ዋጋ ሲሞላ የተጫራቹ ሙሉ ስም፣ ፈርማ፣ ማህተም ያረፈበት አድራሻ፣ ከፍለ ከተማ የቤት ቁጥርና የስልክ ቁጥራቸውን መግለፅ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቶች መ/ቤቱ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከአራት ኪሎ ስፖርት/ስል ማዕከል የፋይናንስ ግዥ/ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት በ500 ብር አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
  8. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በኤንቨሎፒ በማሸግ ተጫራቶች ለሚጫረቱበት መሆኑን እየገለፅን፣ ጨረታውን በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ላይ PLARES ሣጥኑም ታሽጎ በማግስቱ የሥራ ቀን ከሆነ ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ሲሆን የሥራ ቀናት ካልሆነ ደግሞ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በማዕከሉ አዳራሽ ቁጥር 10 በግልፅ የሚከፈት ይሆናል።
  9. ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ድርጅቱን የሚገልፅ ሕጋዊ መታወቂያና ውክልናን የሚገልፅ ደብዳቤ በመያዝ
  10. ተጫራቾች የጊዜውን የጨረታ ሰነድ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒ (copy) አያይዘው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ፋይናንስ ግዥ/ንብረት/ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 8 ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ የጨረታ ሰነድ ከማስገባታቸው በፊት ናሙና የሚጠይቅበት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ካላቀረቡ ከጨረታው ውጪ ይሆናል። ጨረታው በግልፅ ከተከፈተ በኋላ ማንኛውንም መረጃ ዶከመንት/ ማቅረብ
  12. ለአሸናፊዎቹ ክፍያ የሚፈጸመው የተጠየቀውን ዕቃ በተጠየቀውና ባሸነፈው ናሙና መሠረት ሙሉ በሙሉ ወደ ንብረት ክፍል ግቢ ካደረገ በኋላ መሆኑን እናሳውቃለን።
  13. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ የትራንስፖርት አገልግሎት መ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማስገባት ይጠበቅበታል።
  15. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ ላይ ሲፒኦ/ CPO ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  16. ተጫራቾች ከአሸነፉ በኋላ የውል ዋስትና 10% ሲፒኦ (CPO) ከባንክ የተረጋገጠ ማቅረብ የሚችል።

አድራሻ፡- አራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ቢሮ ቁጥር 8 ከሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አጠገብ የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ ስልክ 0111261365

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስተዳደር የአራት ኪሎ ስፖርት፣ ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል

✨ messages.ai_summary
Arat Kilo Sports, Education and Training Center seeks suppliers to provide food ingredients for one year. Bidders must hold a valid renewed business license in the sector, tax payment proof, TIN, VAT registration, and supplier registration with the Finance and Economic Development Office. Samples required.
Save Tender