Tender Detail

Tender Details

  • Company በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ, Phone: 0118883400
  • Website
  • Deadline05 Oct 2026, 5:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 300 (የማይመለስ) በአንድ ሎት
  • Bid Securityሎት 1 ብር 2,340.00; ሎት 2 ብር 50,899.20; ሎት 3 ብር 6,407.20; ሎት 4 ብር 5,580.00 እና ብር 5,580.00; ሎት 5 ብር 806.70; ሎት 6 ብር 2,703.60; ሎት 7 ብር 29,603.29; ሎት 8 ብር 38,791.08; ሎት 9 ብር 49,392.89; ሎት 10 ብር 63,489.67 (በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ)
  • opening dateበአስራ አንደኛው ቀን 4፡30
  • Categories Food And Beverage , Maintenance And Repair , Office Supplies And Services

ሎት 3 የትራንስፖርት አገልግሎት (ሕዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ መካከለኛ፣ የሕዝብ ትራንስፖርት አነስተኛ ሚኒባስና የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ መኪናዎች) እና የጉልበት አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6,407.20

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር

  1. ሎት 1 የመስተንግዶ አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2,340.00
  2. ሎት 2 የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,899.20
  3. ሎት 3 የትራንስፖርት አገልግሎት (ሕዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ መካከለኛ፣ የሕዝብ ትራንስፖርት አነስተኛ ሚኒባስና የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ መኪናዎች) እና የጉልበት አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6,407.20
  4. ሎት 4 የጥገና አገልግሎት (የቢሮ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናና የፈርኒቸር ጥገና) የፈርኒቸር ጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,580.00 እና የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,580.00
  5. ሎት 5 ህትመት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 806.70
  6. ሎት 6 ሞንታርቦና ዲኮሬሽን አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2,703.60
  7. ሎት 7 ቋሚ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 29,603.29
  8. ሎት 8 አላቂ የቢሮ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 38,791.08
  9. ሎት 9 ደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 49,392.89
  10. ሎት 10 የፅዳት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 63,489.67

በጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም የሥራ ዘመን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን አላቂ የቢሮ እቃዎችን፣ የመስተንግዶ አገልግሎት እንዲሁም የቋሚ ዕቃዎች፣ ህትመት፣ ደንብ ልብስ፣ የትራንስፖርትና ጉልበት አገልግሎት፣ ሞንታርቦና ዲኮሬሽን አገልግሎትና የጥገና አገልግሎት ግዢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በመንግሥት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግቦ በፌዴራል ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የምስከር ወረቀት ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉና ንግድ ስም ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የግብር ከፋይነትና የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ከግብር ዕዳ ነፃ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም የሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ቫትን ጨምረው መሙላት አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ በአንድ ሎት 300 ብር በመከፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) የሥራ ቀናት ከዚህ በላይ በተጠቀሰው የቢሮ ቁጥር በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ናሙና ወይም ሳምፕል ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ናሙናና ሳምፕል ለማቅረብ የማይመቹ ዕቃዎችን በፎቶግራፍ እንዲሁም በካታሎግ አጉልቶ በሚያሳይ መቅረብ አለባቸው፡፡
  6. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡ በሥራ ዕድል ጽ/ቤት የተደራጁ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት አምራች በሆኑበት ሥራ ዘርፍ ብቻ ነው፡፡
  7. ገዢው አካል የሚገዛውን ዕቃ እስከ ሃያ ፐርሰንት (20%) ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  8. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በኤንቨሎፕ በማሸግ ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ከላይ በተዘረዘረው በየሎቱ መሠረት የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በተራ ቁጥር 4 በተጠቀሰው አድራሻ መሠረት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ለአሸናፊዎችና ተሸናፊዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራቶች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም ማሸነፋቸው ከታወቀ ከሰባት ቀናት በኋላ ቀርበው በሰባት ቀናት ውስጥ የጠቅላላው ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% (አስር ፐርሰንት) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ አሠርተው ውል መዋዋል አለባቸው፡፡
  11. ጨረታው በአስረኛው ቀን ላይ ተዘግቶ በማግስቱ በአስራ አንደኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ቢሮ ቁጥር 1 አንደኛ ፎቅ ፋ/ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- መካኒሳ እሚጎ ካፌ 500 ሜትር ከፍ ብሎ ብሎ በሚገኘው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 02 አስተዳደር ቅጥር ግቢ ውስጥ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0921547457/0918973904/0910256792/0910225112

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The buyer seeks transport services (public transport minibuses, mid-size and freight vehicles) and labor services under Lot 3. Bidders must be registered government suppliers with a Federal Procurement and Property Administration Agency certificate, renewed business license, tax clearance, VAT registration, and submit samples or photos/catalogs.
Save Tender