የደ/ም/ኢ/ህ/ከ / መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ/ም በጀት ዘመን ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት በካፋ ዞን የቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መስያ ቁጥር 001/2019
የደ/ም/ኢ/ህ/ከ / መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ/ም በጀት ዘመን ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ማለትም፤ በሎት 1 የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ በሎት 2 ሆቴልና ቱርዝም እቃ፣ በሎት 3 አግሮ ፕሮሰስንግ እቃ ፤ በሎት 4 አይሲቲ እቃዎች፤ በሎት 5 የጋርሜንት እቃዎች፤ በሎት 6 አውቶሞቲቪ እቃዎች፤ በሎት 7 ኤሌክትሪክ እቃዎች፤ በሎት 8 ሰርቤይንግ እቃዎች እና በሎት 9 እስቴሽኔሪ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፣ ተወዳዳሪዎች፡-
- በሙያ መስክ ወይም በዘርፉ የተመዘገቡና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው፣ ህጋዊ ዕቃ አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይ ስለመሆናቸው እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ /specification/ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአ/አበባ መከሲኮ አከባቢ ከሚገኘው ተግባረእድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መግቢያ በር በአካል በመቅረብ በኮሌጁ የሂሳብ ቁጥር 1000029122877 ላይ የማይመለስ 300 ብር በማስገባት የመጫረቻ ሰነዱን መውሰድ ትችላላችሁ ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው የሚታሸግበትና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት የምጫረቱባቸውን እቃዎች በመለየት በአይነታቸው እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤምቬሎፕ ለየብቻ ዋናውንና ኮፒውን በፖስታ በማሸግ የሚጫረቱበትን ዘርፍ የተጫራቾችን ስም ወይም ድርጅት በመፃፍና ማህተም በመምታት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በሰዓቱ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አ/አበባ መከሲኮ አከባቢ ከሚገኘው ተግባረእድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መግቢያ በር ከረፋዱ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም በጨረታ መዝጊያና መከፈቻ ወቅት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል ያለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አይከለከልም። እለቱ የእረፍት ወይም በዓል ቀን ከሆነ ወደ የሚቀጥለው ስራ ቀን ይተላለፋል፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፣ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተርአፍ ክሬዲት ለያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማወዳደርያ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ቴክኒካል ሰነድ ውስጥ በማሸግ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በጨረታ የተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- አሸናፊዎች ባሸነፉበት የዕቃ ዋጋ መጠን የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ የተረጋገጠ CPO፣ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተርአፍ ክሬዲት ለያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማወዳደርያ ሰነድ ለየብቻ ማስያዝ እና ያሸነፉበትን የእቃ ናሙና ውል ከገቡበት 3/ሶስት/ ቀን ውስጥ ለኮሌጁ ቀድሞ ማቅረብ ይኖርባችዋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ዕቃውን እስከ ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድረስ የትራንስፖርትና ማንኛውንም ወጪ በመቻል በውሉ ላይ በሚጠቀሰው ቀን ማቅረብና ማስረከብ አለባቸው፡፡ ለማያቀርቡት ለውል ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ አይመለስም፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከተከፈተበት እለት ጀምሮ ለ60 ቀናት ይሆናል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ማንኛውንም ማስተካከያ ማድረግም ሆነ ከቀረበው ሰነድ ውጭ መሙላት አይፈቀድም።
- ተጫራቾች ባሸነፉበት እቃ የካሽ ሪጅስቴር ደረሰኝ ከአታችሜንት ጋር አያይዞ ማቅረብ ወይም የካሽ ሪጅስቴር ደረሰኝ የማይጠቀሙ ከሆነ የማይጠቀሙበት ምክንያት ከገቢዎች መ/ቤት ደብዳቤ በማስደገፍ የእጅ በእጅ ደረሰኝ ጋር ማቅረብ አለባችሁ።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0917916439 /0913466023 /0927694591/ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ / መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
✨ messages.ai_summary
Bonga Polytechnic College seeks suppliers for training materials across nine lots: construction, hotel/tourism, agro-processing, ICT, garment, automotive, electrical, surveying, and stationery equipment. Bidders must hold a valid trade license, tax clearance, supplier registration, and VAT status.
