Tender Detail

Tender Details

  • Company የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንትርፕራይዝ
  • Address ጎንደር ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0908085555
  • Website
  • Deadline05 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Security1%
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ 16 ቀን ቆይቶ በ 16 ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Food Items And Drinks , Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ለእቴጌ ምንትዋብ ሞዴል መድሀኒት ቤት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መድሀኒቶች፣ የንጽህና መጠበቂያዎች፣ ተጨማሪ የህጻናት ምግቦች እና የህከምና ግብዓት እቃዎችን በዘርፉ ንግድ ፈቃድ አውጥተው ከተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንትርፕራይዝ


የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር E/M/T/C/E/NCB/01/2019

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ለእቴጌ ምንትዋብ ሞዴል መድሀኒት ቤት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መድሀኒቶች፣ የንጽህና መጠበቂያዎች፣ ተጨማሪ የህጻናት ምግቦች እና የህከምና ግብዓት እቃዎችን በዘርፉ ንግድ ፈቃድ አውጥተው ከተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

1. በዘረፉ የወጣና ለዘመነ የንግድ ስራ ፈቃድ ኮፒ፣ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ኮፒ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ሰርትፊኬት ኮፒ፣ በማንኛውም የመንግስት ግዥ ጨረታ ሰርትፍኬት እንዲሳተፉ በሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የተሰጠ ድጋፍ ደብዳቤ ኮፒ ፈርመውና በድርጅታቸው ማህተም አረጋግጠው ዋናውን ማቅረብ አለባቸው፡፡

2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 1% ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንከ በሚስጥ ሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በእቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ስም አሰርተው ማቅረብ ( አለባቸው፡፡ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ከ90 ቀን በታች መሆን የለበትም፡፡

3. ተጫራቾች በተ.ቁ 1 እና 2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ እንዲሁም የዋጋ መወዳደርያ ስነዳቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግና በማያሻማ ሁኔታ በጀርባው ላይ ኦርጅናልና ኮፒ በሚል ቃል በጽሁፍ በማመላከትና በድርጅታቸው ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡

4. ሁሉም (ሶስቱም) ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ ተጠቃለው ታሽገውና በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጠው መግባት አለባቸው።

5. ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከርኢንተርፕራይዝ ፋይናንስና አስተዳደር ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 06 የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደርያ ስነዳቸውን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠርእስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ስዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታውም ታዛቢዎችና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት 4፡01 ታሽጎ በእለቱ 4፡30 እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከርኢንተርፕራይዝ ይከፈታል፡፡

7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ቢያንስ 90 ቀን ድረስ ጸንቶ መቆየት አለበት፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎችን ታከስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋ ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ የታከስ ሁኔታ ያልተገለጸ ከሆነ የተሞላው ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ታክስና ወጭን አካቶ እንደተላከ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡

9. ተጫራቾች ወይም አቅራቢዎች ዋጋውን የሚሞሉት ከአከፋፋዮች ከገዙበት ዋጋ ላይ በተፈቀደላቸው የትርፍ ህዳግ መሰረት በፐርሰንት ዋጋ የሚሞሉ ይሆናል

10.ተጫራቾች ዋጋውን ሲሞሉ ከአስመጭዎች የገዙበትን የዋጋ ዝርዝር ህጋዊ፣ ግልጽ፣ የሚነበብና የሚታይ መረጃ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ።

1.ተጫራጮች በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ በቀጣይ የሁለት (2) ዓመታት በወቅቱ በሚኖረው የገበያሁኔታመድሀኒቶችን እና የህከምና ግብዓት እቃዎችን ለማቅረብ የኮንትራት ውል ስምምነት (contractual agreement) ለመውሰድ ፈቃደኛ መሆን እና ዋጋው ሲቀንስ አትራቢዎች ሊቀንሱ ዋጋው ሲጨምር ደግሞ ኢንተርፕራይዙ ሊጨምርየሚስማሙ መሆን አለባቸው፡፡

12.ተጫራጮች በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ ከተዘረዘሩት መድሀኒቶችና ህከምና ግብዓቶች አይነቶች ውስጥ ቢያንስ 25% በላይ ማቅረብ አለባቸው፡፡

13. ኢንተርፕራይዙ አሁን ከጠቀሳቸው መድሀኒቶችና የህክምና ግብዓት እቃዎች በተጨማሪ በቀጣይ ለመግዛት ቢፈልግ አሸናፊ አቅራቢዎች አሁን ባቀረቡት መድሀኒቶችን፣ ህከምና ግብዓቶችን እና ተጨማሪ የህጻናት ምግቦችን ባሸነፉበት መስፈርት አሁን በዝርዝሩ ያልተጠቀሱትን ሌሎችንም ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆን ይኖርባቸዋል።

14. አሸናፊ አቅራቢዎች የሚያቀርቧቸው መድሀኒቶችና የህከምና ግብዓቶች የመጠቀሚያ አገልግሎት ጊዜያቸው (expire date) ከአንድ ዓመት በላይ የቀረው መሆን አለበት፡፡

15.ኢንተርፕራይዙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

16. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልከ ቁጥር 0918777942 ወይም 0918053797 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ

✨ messages.ai_summary
Gondar University Etege Mintiwab Enterprise seeks licensed suppliers for medicines, hygiene supplies, supplementary child foods, and medical supplies for Etege Mintiwab Model Drug Store via open bid. Bidders need a valid trade license, TIN, VAT certificate, and a domestic supplier support letter.
Save Tender