በጉለሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 08 የደጅአዝማች በላይ ዘለቀ ቁ.2 ቅ/አንደኛ፣ እንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ለ2019 ዒ.ም ልዩ ልዩ የትምህርት ግብዓቶችን እና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ በመደበኛ በጀት እና በውስጥ ገቢ በጀት አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የደጅአዝማች በላይ ዘለቀ ቁ.2 ቅ/አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
የመጀመሪያ ዙር የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር/001/2019
በጉለሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 08 የደጅአዝማች በላይ ዘለቀ ቁ.2 ቅ/አንደኛ፣ እንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ለ2019 ዒ.ም ልዩ ልዩ የትምህርት ግብዓቶችን እና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ በመደበኛ በጀት እና በውስጥ ገቢ በጀት አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የጨረታ ማስከበሪያ CPO
ሎት- የደንብ ልብስ ብር 5000፣ ሎት-2 የደንብ ልብስ ስፌት ብር 1000፣ ሎት-3 የፅዳት እቃዎች ብር 5000፣ ሎት-4 የህትመት ስራዎች ብር 1000፣ ሎት 5 አላቂ የህከምና እቃዎች ብር 500፣ ሎት-6 አላቂ የትምህርት እቃዎች ብር 2500፣ ሎት-7 እስቴሽነሪ /የፅህፈት/መሣሪያዎች ብር 4000፣ ሎት-8 እጋዥ መፅሐፍት ብር 500፣ ሎት-9 የኤሌትሪክ፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የተለያዩ የቧንቧ እቃዎች ብር 2000፣ ሎት-10 ቋሚ እቃዎች ብር3200፣ ሎት-11 የጥገና ስራዎችን ብር 3000፣ ሎት-12 የትራንስፖርት አገልግሎት ብር500 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት በባንከ የተረጋገጠ CPO ማሲያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- አግባብነት ያለው ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡ ከፋይናንስ ሚ/ርበአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በሚወዳደሩበት እቃ ልዩ አስተያየት እንዲደረግለት ከፈለገ የአምራችነት ወይም እሴት የጨመረበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ከቢሮ ቁ.5 መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው 10ኛው ቀን 11፡30 ተዘግቶ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቾቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ መግለጫ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁ.5 ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች መጫረት የሚችሉት በንግድ ፍቃድ ዘርፍ ብቻ መሆን አለበት ፡፡
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ እቃ ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቅድሚያ ያላቀረቡ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጪ ይሆናሉ፡፡
- አሸናፊው በአሸነፈባቸው እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ት/ቤቱ ንብረት ከፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ጨረታ ላይ ከተጠቀሱት እቃዎች ብዛት ት/ቤቱ ከውል በፊት 20% መጨመር ወይም 20 % መቀነስ ይችላል፡፡
አድራሻ፡- አዲሱ ገበያ ከፍ ብሎ ፂዮን ሆቴል ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0111270985 / 0111547428 እና 0111547484 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የደጅአዝማች በላይ ዘለቀ ቁ.2 ቅ/አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
