Tender Detail

Tender Details


በለሚ ኩሪ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የጨፈ የመጀ/ደ/ት/ ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በአንደኛ ዙር የተሰያዊ የደንብ ልብስ አላቂ የቢሮና የት/ት ዕቃዎች የኤሌክትሮኒክስ እና የህንጻ መሳሪያ ዕቃዎች፣ የስፖርት ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለፈለገ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወደሚገለጸው ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

ጨፌ የመጀ/ደ/ ት/ ቤት


የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018

በለሚ ኩሪ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የጨፈ የመጀ/ደ/ት/ ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በአንደኛ ዙር የተሰያዊ የደንብ ልብስ አላቂ የቢሮና የት/ት ዕቃዎች የኤሌክትሮኒክስ እና የህንጻ መሳሪያ ዕቃዎች፣ የስፖርት ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለፈለገ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወደሚገለጸው ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

የሎት ቁ የሎት ዝርዝር የብር መጠን
ሎት.1 የደንብ ልብስ 56,500.00
ሎት.2 አላቂ የት/ት እና የቢሮ ዕቃ 50000.00
ሎት.3 የኤሌክትሮኒክስ እና የሕንጻ ዕቃዎች 39,000.00
ሎት.4 የስፖርት ዕቃዎች 6,000.00
ሎት.5 አላቂ የጽዳት ዕቃዎች 45,000.00
ሎት.6 ኮምፒውተር እና የኮምፒውተር ዕቃዎች አክሰሰሪዎች 34,200.00
ሎት.7 የቀይ መስቀል ዕቃዎች 10000.00
ሎት.8 የላብራቶሪ ዕቃዎች 5,000.00
ሎት.9 የሙዚቃ መሣሪያ ዕቃዎች 10000.00
ሎት.10 ፈርኒቸር 10000.00

በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ፡-

  1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው በመንግስት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
  3. የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት፡፡
  4. ተጫራቹ በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው መሆን አለበት፡፡
  5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በጨፈ የመጀ/ደ/ት/ቤት ስም በባንክ በተመሰከረለት ሲፒአ (CPO) ለእያንዳንዱ ለሚሳተፉበት ሎት ማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡
  6. የጨረታ ጊዜ ጸንቶ የሚቆየው 45 ቀን ብቻ ነው፡፡
  7. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ከት/ቤቱ የፋይናንስና ግዢ/ን/ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 04 የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ/ ለከ ሎት የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በመከፈል መውሰድ ትችላላችሁ፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ተጫራቾች ለሚያመርቱት ምርት ብቻ ከክፍያ ነጻ ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ በማጻፍ እና ለማያመርቱት ምርት /ዕቃ/ እንደ ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን በመግዛት እና በየሎቱ የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ ጨረታውን መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  8. አማራጭ የጨረታ ሀሳብ ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃዉን በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ የመሥሪያ ቤቱን ንብረት ከፍል ድረስ ማስገባት እና ማስረከብ አለበት፡፡
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  11. ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዶችን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ከማስረጃዎች ጋር በማደራጀት በታሸገ ፖስታ ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  12. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ10ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ በቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 10ኛው ቀን በዓል የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታ እና ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ዘግይተው ወይም 10ኛው ቀን 8:00 ሰዓት በኋላ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸዉም፡፡
  14. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ እንደ ተገለጸለት የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ ዋስትና ማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡
  15. ተጫራቹ ባሸነፉበት የዕቃዎች ብዛት ላይ መስሪያ ቤቱ 20% ወደ ላይ 20% ወደ ታች አድርጎ መግዛት ይችላል፡፡ እንዲሁም ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፦ ከመገናኛ አያት ኮንደሚኒየም ቁጥር 1 ጸበል መድኃኒዓለም ፖሊስ ጣቢያ በታከሲ ተራ ገባ ብሎ ስልክ ቁጥር 0116-39-18-17

ጨፌ የመጀ/ደ/ ት/ ቤት

✨ messages.ai_summary
Chefe Primary School invites eligible suppliers to bid for uniforms, consumable office and teaching materials, electronics, building supplies, sports, cleaning and first-aid items, laboratory and music equipment, computers and furniture. Bidders need a valid trade licence, VAT registration, supplier certificate and must submit samples.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender

በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሎት-1 -ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት-2፡ - የፅዳት ዕቃዎች ፣ሎት-3 የደንብ ልብስ፣ሎት-4 የተሽከር...

READ MORE
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት ለማሟያ የሚሆን በአንደኛ ዙር ያልተከናወኑ የሁለተኛ ዙር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደ...

READ MORE