Tender Detail

Tender Details


በአራዳ ከ/ከተማ የዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛና መካከኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ቡድን የ2019 በጀት አመት ከኛ ዙር ግልፅ ጨረታ የሚያስፈልገውን:-

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ት/ጽ/ቤት የዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

በአራዳ ከ/ከተማ የዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛና መካከኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ

ቡድን የ2019 በጀት አመት ከኛ ዙር ግልፅ ጨረታ የሚያስፈልገውን:-

ሎት 1 የደንብ ልብስ

ሎት-2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች

ሎት-3 አላቂ የትምህርት እቃዎች

ሎት-4 የተለያዩ መሳሪያዎች

ሎት-5 የፕላንት ማሽነሪ እና መሣሪያ መግዣ

ሎት-6 የደንብ ልብስ ስፌት

ሎት-7 ቋሚና አላቂ ጽዳት እቃዎች

ሎት-8 ህትመት

ሎት-9 ለህንጻና ቁሳቁስ ለተገጣጣሚዎች መግዣ

ሎት-10 ፕላንት ማሽነሪ ጥገና

ሎት-11 ለህንጻና ቁሳቁስ ለተገጣጣሚዎች እድሳት ዕቃዎች መግዣ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች ቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸውና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ፍቃድ ማስረጃ ያላቸው TIN NO የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2. በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል እና በመንግስት ግዥ ያልታገዱ፡፡

3. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በፖስታ አሽገው ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10(አስር ) የስራ ቀናት ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል ሎት 1፣2 እና 3 ብር 10,000.00(አስርሺህ ብር) ፣ሎት 4 እና 5 የመጫረቻ ዋጋ ብር 12,000.00(አስራ ሁለት ሺህ ብር) ፣ሎት 6 ፣7 እና 8 የመጫረቻ ዋጋ ብር 8,000.00(ስምንት ሺህ ብር) እና ሎት 9 ፣10 እና 11 የመጫረቻ ዋጋ ብር 9,000.00(ዘጠኝ ሺህ ብር በሕጋዊነት ከተረጋገጠ ባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ) ብቻ በመከፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር ) ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ የፋይናንሻል ኦርጂናል እና እንዲሁም የቴክኒካል የኦርጅናል ኮፒ በመለየት ተሟልቶ በማሸግ ፊርማና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ፖስታው ላይ አድራሻ ተጽፎ ቢሮ ቁጥር 10 (አስር) በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ት/ቤቱ ካዘጋጀው የዋጋ መሙያ ውጪ ሌላ ቅፅ መጠቀም ከጨረታ ውድድር ውጪ ያስደርጋል፡፡

6, ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡30 (አራት ተኩል ) ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ እለቱ በዓል ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡

7. ናሙና ያልቀረበበት የዘገየ የጨረታ በመከፈት ሂደት ላይ ያልተነበበ ጨረታ እንዲሁም የጨረታ ሰነድ ተሟልቶ ያልመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ በጨረታ ሰነድ ክፍል 4.6.9 የተቀመጡት ግዴታዎች ከሰነዱ ጋር ተሟልተው ያላቀረቡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

8. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዣ እና ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዢ ፈጻሚው መ/ቤት መጋዘን ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

9. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚያቀርቡት እቃ እንደ ማነኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አይጠበቅባቸውም፡፡

10. ስርዝ ድልዝ መረጃዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ መስሪያ ቤቱ ለግዢው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ:‐ስራት ኪሎ ሚኒሲክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ጎን ከሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ገባ ብሎ እንገኛለን፡፡

የት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ስ.ቁ 011-23-28-66

ዳግማዊ ሚኒሊክ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት

 

✨ messages.ai_summary
Dagmawi Minilik Primary and Middle School seeks suppliers for 11 lots: uniforms, office and educational consumables, various equipment, plant machinery purchase and maintenance, cleaning supplies, printing, and building materials. Bidders must be tax-registered, have a valid license, and be registered with the government procurement agency.
Save Tender