በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬህክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ በኢንዱስትሪው ውስጥ ያለ 32 (ሰላሳ ሁለት) ስማርት ኤሌክትሪክ ፖል መብራቶችን ከነ ሙሉ አከሰሰሪው ለማሰራት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በአገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨ.ሰ.ቁ፡- ቢ.ሞ.ቬ.ኢ.ኢ/ብ.ግ.ጨ.ሰ/01/2018
በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬህክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ በኢንዱስትሪው ውስጥ ያለ 32 (ሰላሳ ሁለት) ስማርት ኤሌክትሪክ ፖል መብራቶችን ከነ ሙሉ አከሰሰሪው ለማሰራት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በአገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከታች የተገለፀውን ዝርዝር መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1) በዘርፍ የተሰማሩበት ህጋዊ የሆኑ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፤የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
2) ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ በፋይናንስ በኩል የጨረታ ሰነዱን በብር 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ከፍለው በመውሰድ ለጨረታ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን እና የምትወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ኦርጅናል ዐi(አንድ) እና ኮፒ ዐi(አንድ) ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
3) ማንኛውም ተጫራቾች በሚቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የሕጋዊ ወኪሉ ስም ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መስፈር አለበት፡፡
4) ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንከ የተመሰከረለት የጨረታ ማስከበሪያ CPO፣በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
5) ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በግልፅ በኢትዮጵያ ብር ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በዝርዝርማስፈር አለባቸው፡፡ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታከስ ያካተተ መሆኑንና አለመሆኑ መገለፅ አለበት፡፡
6) አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈራረሙ የውል ማስከበሪያ ዋስትና (Performance Bond) ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ ከፍያ ማዘዣ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም ውል ከተፈራረሙ በኋላ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወዲያውኑ ይለቀቅላቸዋል፤
7) ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በኢንዱስትሪው ቅጥር ግቢ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ሳጥኑ ከሚዘጋበት ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
8) ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከዋናው ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅቢያ ሰንጠረዥ መሰረት በጥራትና በተቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሠረት ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
9) በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራች ከኢንዱስትሪው ጋር የሥራ አፈፃፀም ውል መፈራረም አለበት ውል ካልፈረመ ያስያዘው 2% (CPO) ተወርሶ ለኢንዱስትሪው ገቢ ይደረጋል ::
10)ጨረታው የሚከፈተው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ተከታታይ የስራ ቀናት ጀምሮ በዘኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሾፍቱ ሞተር ቬህክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ቀኑ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይበተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፤
11)ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0994521556/0900271710 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፤
12)ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው::
አድራሻ፡-ቢሾፍቱ ሞተር ቬህክስስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ቢሾፍቱ/ደብረ ዘይት ስልክ
ቁጥር :0994521556/0900271710
በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ
