የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስፖርት ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ለስፖርት ኮሚሽን ሎት 1 ለስፖርት ምክር ቤት ግቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ግዥ፣ ሎት 2 ለሀገረ-ሰላም አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 60 ለሰልጣኞች የምግብ አቅርቦት በድጋሚ በማውጣት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
idama National Regional State Sports Commission
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስፖርት ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ለስፖርት ኮሚሽን ሎት 1 ለስፖርት ምክር ቤት ግቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ግዥ፣ ሎት 2 ለሀገረ-ሰላም አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 60 ለሰልጣኞች የምግብ አቅርቦት በድጋሚ በማውጣት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) እየከፈሉ ከመ/ቤቱ ግዢ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን 10,000 (አስር ሺህ) በጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ጨረታው በሁለት ፖስታ የሚቀርብ ሲሆን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ መቅረብ አለበት። ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 15ተኛዉ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ በ10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ስማቸውንና ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውንና ስልክ ቁጥር ማስፈር አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የግዥውን ብዛት /መጠን/ እንደአስፈላጊነቱ እስከ 20% ለመቀነስ /ለመጨመር/ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የደረሰኝ አይነት እና ምግብ አይነት መ/ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን ዝርዝር መሰረት ብቻ ነው መወዳደር የሚችሉት።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- 0462216730/0919155930 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
የመ/ቤቱ አድራሻ ሀዋሳ ከተማ ቀድሞ ሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ቅጥር ግቢ፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስፖርት ኮሚሽን
✨ messages.ai_summary
Supply of receipt collection materials for the Sports Council compound (Lot 1) and food supply for 60 trainees at the Hagereselam Athletics Training Center (Lot 2). Bidders must have a renewed business license, tax registration, and VAT registration if bid exceeds 500,000 birr.
