የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የተለያዩ የቀላል ተሽከርካሪዎች ጎማ ግዥ ለማከናወን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEU-PPM/03/2019(NCB)
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የተለያዩ የቀላል ተሽከርካሪዎች ጎማ ግዥ ለማከናወን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታ መወዳደር ይችላሉ ፡፡
| የዕቃው ዓይነት | ሎት | የጨረታ ማስከበሪያ መጠን | ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት | ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት |
| የቀላል ተሽከርካሪ ጎማ | 1. | 200,000.00 | መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም. 8:00 ሰዓት | መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት |
| 2 | 250,000.00 | |||
| 3 | 170,000.00 |
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፤ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው ፤
- የጨረታ ሰነዱን መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል የኢኤአ ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ከካቴድራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬከ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ዋስትና የንግድ ማዕከል ከኛ ፎቅ ቢርቁጥር 106 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ሎቶች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በተገለጸው የብር መጠን መሰረት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለውን የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በኢ.ኤ.አ. አአአ.አፕ ወይም EEU-UEAP ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EEU-PPM/03/2019 (NCB) የሚል ምልከት በማድረግ እና የሎት ቁጥሩን በመፃፍ ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተገለጸው አድራሻ እስከ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም መስከረም 26 ቀን 2019 ከቀኑ 8፡30 ላይ ይከፈታል።
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት 7፡00-11፡00 እና ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይችላሉ ፡፡
- የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011263159 መደወል ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Electric Utility's Project Portfolio Management Office seeks eligible suppliers for the supply of tires for various light vehicles via open tender. Bidders must be legally licensed in the field, provide proof of tax payment and VAT registration.
