Tender Detail

Tender Details

  • Company የመድኃኔዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ ብሎ ቶታል ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-2-59-55-94
  • Website
  • Deadline28 Sep 2026, 4:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 200 (non-refundable)
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateተከታታይ 10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather

በጉለሌ ክ/ከተማ የመድኃኔዓለም አጠ/2ኛ ደረ/ት/ቤት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ የሚከተሉትን ዕቃዎች ግዢ መፈጸም ይፈልጋል።

የመድኃኔዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- መድ/አጠ 2ኛ/ደረ/ት/ቤት 02/2019 ዓ/ም

በጉለሌ ክ/ከተማ የመድኃኔዓለም አጠ/2ኛ ደረ/ት/ቤት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ የሚከተሉትን ዕቃዎች ግዢ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

  • ሎት 1 ለጽህፈት እና ለትምህርት መሳሪያዎች 34,144.26ብር /ሰላሳ አራት ሺህ አንድ መቶ አርባ አራት ብር ከሀያ ስድስት ሳንቲም/
  • ሎት 2 ለጽዳት ዕቃዎች 20,000 ብር /ሀያ ሺህ ብር/
  • ሎት 3 ለደንብ ልብስ ዕቃዎች 62,400 /ስልሳ ሁለት ሺህ አራት መቶ ብር/
  • ሎት 4 ለአላቂ የህክምና ዕቃዎች 400ብር /አራት መቶ ብር/
  • ሎት 5 ለኤሌክትሪክ እና ለህንጻ እቃዎች 12,955.74ብር /አስራ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ አምስት ብር ከሰባ አራት ሳንቲም/
  • ሎት 6 ለስፖርት ዕቃዎች 1,000 ብር /አንድ ሺህ ብር/
  • ሎት 7 ለደንብ ልብስ ስፌት 1,000 ብር /አንድ ሺህ ብር/
  • ሎት 8 ለቋሚ ዕቃዎች 10,000 ብር /አስር ሺህ ብር/
  • ሎት 9 ለጭነት እና ጉልበት አገልግሎት 10,000 ብር /አስር ሺህ ብር/
  • ሎት 10 የትምህርት ቤቱን ከበብ ለማከራየት 55,123.20/ሀምሳ አምስት ሺህ አንድ መቶ ሀያ ሶስት ብር ከሀያ ሳንቲም/
  • ሎት 11 የግቢ ውስጥ ጥገናዎች 21,000ብር /ሀያ አንድ ሺህ ብር/

በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በማስያዝ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፣

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር የከፈለ
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  3. ተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  4. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  5. በሁለትና ከዛ በላይ ሎት ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ለእያንዳንዱ ሎት የተሟላ ማስረጃ በማያያዝ በተለያዬ ፖስታ በማሸግ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን የተሟላ ማስረጃ የሌለው ሎት ውድቅ ይሆናል።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
  7. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ከት/ቤቱ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 17 በሎት የማይመለስ ብር 200 በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ።
  8. በመንግስት የተደራጁ ልዩ አስተያዬት የሚደረግላቸው ድርጅቶች በድጋፍ ደብዳቤ መሳተፍ የሚችሉት እራሳቸዉ ባመረቱት እቃዎች ላይ ብቻ ነው።
  9. ት/ቤቱ ከሚገዛው ዕቃ ግዢ ላይ ከውል በፊት 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
  10. አሸናፊው ድርጅት ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ አለበት።
  11. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ እስከ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማድረስ አለበት።
  12. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ በወሰዱት ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ ዋጋውን በመሙላት የግዢውን አይነትና የድርጅቱን ሙሉ ማስረጃ የታሸገው ፖስታ ላይ በመጻፍ ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታ ላይ የድርጅት ማህተብና ፊርማ በማስቀመጥ ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  13. ለሚያቀርቡት ዕቃዎች ፖስታውን ስያስገቡ ናሙና ለሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙናዎች መግባት አለባቸው።
  14. ትምህርት ቤቱ ካስቀመጠው ተፈላጊነት /specification/ አንሰው ወይም በልጠው የሚመጡ ናሙናዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  15. ጨረታው በ 10ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት የከፈታል።
  16. ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ያሸነፈውን ጠቅላላ የዕቃዉን መጠን 25% እስከ 6 ወር ድረስ ተጨማሪ ቢጠየቅ በራሱ ዋጋ የሚያቀርብ ይሆናል።

ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። የመድኃኔዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ ብሎ ቶታል ፊት ለፊት ይገኛል።

ስልክ: 0112 593 437 / 0112 593 438

በጉለሌ ክ/ከተማ የመድኃኔዓለም አጠ/2ኛ ደረ/ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Medhanealem General Secondary School seeks legal bidders for supplies and services across 11 lots: stationery and teaching materials, cleaning supplies, uniforms, medical consumables, electrical and building materials, sports equipment, tailoring, fixed assets, transport and labour, canteen rental, and compound maintenance.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender

በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሎት-1 -ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት-2፡ - የፅዳት ዕቃዎች ፣ሎት-3 የደንብ ልብስ፣ሎት-4 የተሽከር...

READ MORE
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት ለማሟያ የሚሆን በአንደኛ ዙር ያልተከናወኑ የሁለተኛ ዙር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደ...

READ MORE