የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ ስራዎችን እና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ ስራዎችን እና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት፡- ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፤
| Lot No. | Item |
| 1. ሎት 1 | Tourism information System |
| 2. ሎት 2 | Digital Promotion and Content Development |
| 3. ሎት 3 | Virtual Reality |
| 4. ሎት 4 | ኤልድ እስክሪን ግዥ/Digital Screen (LED) |
- በጨረታ ቁጥር አ.አ.ቱ ኮ.ግ ጨ.002/2019 በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ፤-
- ቢሮ ቁጥር 706 የማይመለስ ብር የእንዱ የሰነዱ መግዢያ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመከፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የገቢዎች ክሊራንስ ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምዝገባ ሰርትፍኬት ማቅረብ የሚችሉና ፣በግዥ አቅራቢነት የተመዘገቡ፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት እያንዳንዱ ሰነድ እና ፖስታ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማቸውን ማኖር ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ለሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ - 25,000.00 ብር ለሎት 2፡ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 ብር ለሎት 3- የጨረታ ማስከበሪያ -20,000.00 ሎት 4 የጨረታ ማስከበሪያ፤100,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤ ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 701 በሚገኘው በኮሚሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት - የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 701 በሚገኘው በኮሚሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡ የመከፈቻው ዕለት በዓል/ዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋናውንና ኮፒውን / ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ፣ ፋይናንሽል ኦሪጂናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- በጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ከመ/ቤታችን ጋር ጨረታውን እንዳሸነፈ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ በሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል፡፡
- ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን
