Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት
  • Address Addis Ababa Ethiopia, Phone: 09 30 48 90 18
  • Website
  • Deadline10 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 300 (ሦስት መቶ ብር)
  • opening dateለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በአሥራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Categories

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት ለሠራተኞች መዝናኛ ክበብ የምግብና ተያያዥ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል ይዞ ማስሰራት ይፈልጋል።


የመዝናኛ ክበብ የምግብና ተያያዥ አገልግሎት

ግዥ ግልጽ ጨረታ

ኮ /ዲ /ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ/33/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት ለሠራተኞች መዝናኛ ክበብ የምግብና ተያያዥ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ውል ይዞ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም: -

1.      በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300(ሦስት መቶ ብር) በመከፈል በኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት C.R.D.A አጠገብ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

2.    ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 ብር /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (un- conditional bid bond guarantees) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3.    ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በአሥራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 በግዥ ዳይሬክቶሬት ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

4.    ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 09 21 02 25 81/ 09 12 33 99 77

አድራሻ: ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፌት ከሲ.አር.ዲ.ኤ አጠገብ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት

Save Tender