ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም የእቃዎቹ ዝርዝር ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ ሎት 2 የፅዳትእቃዎች፣ ሲሆኑ ዝርዝሩንና ብዛቱን በጨረታ ሰነዱ ላይ ተጠቅሷል። በዚህ መሠረት ድርጅቱ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ተጫራቾች፡-
1. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ከድርጅቱ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ/ በመክፈል ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 07 መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የቫት መመዝገቢያ ሰርተኬት ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል።
4. የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀው የብር መጠን በባንክ በተመሰከረበለት (CPO) ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
5. ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ ሞልቶ በሚያቀርበው ዋጋ የእያንዳንዱ እቃዎች ብራንዳቸውን፣ ዓይነታቸውና ሌሎች የዕቃው መገለጫዎች በጨረታ ሰነዱ መሰረት መግለጽ ይኖርበታል።
6. ተጫራች ከዚህ ቀደም በተለያዩ ድርጅቶች የጨረታ አሸናፊ በመሆን በተሳተፈባቸው የመልካም የስራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።
7. ተጫራቾች ለመወዳደር በሎት የተገለፁት በመረጡት ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርበታል።
8. በጨረታው መሰረት ተጫራቹ አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች አሽናፊ መሆኑን ከተነገረበት ቀንጀምሮ በሙሉ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ መሰረት በራሱ መጓጓዣ ስቴድየም ወደ ሚገኘው ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንጻ የይሓ ሪል እስቴት ንብረት ክፍል /11ኛ ፎቅ ድረስ በማጓጓዝ ማስረከብ ይኖርበታል።
9. ለአሸናፊው ድርጅት ግለሰብ የዕቃዎቹን ዋጋ የሚከፈለው ዕቃዎቹን ሙሉ በሙሉ ካስረከበ በኋላ ይሆናል።
10. ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8 /በስምንተኛው የሥራ ቀን በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይሆናል።
11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8 /በስምንተኛው የሥራ ቀን/ በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይሆናል።
12. ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ መገኘት ይችላል።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ስቴድየም ቤተ ዛታ ሆስፒታል ፊት ለፊት “ይሓ ሲቲ ሴንተር” ህንጻ 2ኛ ፎቅ
የቢሮ ስልክ ቁጥር፡ 011 558 0129/03 / 011 557 6954/ሞባይል- 09 22 07 95 75 / 09 11 39 72 39
ማሳሰቢያ:- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
