በጉ/ክ/ከ/ወ/10 የሸጐሌ ጤና ጣቢያ የ2019 ዓ/ም 1ኛ ዙር ጨረታ በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ ለመጫረት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ሸ/ጤ/ጣ/01/2019
በጉ/ክ/ከ/ወ/10 የሸጐሌ ጤና ጣቢያ የ2019 ዓ/ም 1ኛ ዙር ጨረታ በሎት ከፋፍሎ በግልፅ ጨረታ ለመጫረት ይፈልጋል ሎት 1፤ ቋሚ የህክምና ዕቃዎች ሎት 2፤ የላብራቶሪ ሪኤጀንቶችና መድኃኒቶች ሎት 3፤ የፈርኒችር ዕቃዎች ሎት 4፤ ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የኤሌትሪክ ተዛማጅ እቃዎች ሎት 5 EMRS MATERIALS 6፤ የህትመት ውጤቶች ሎት 7፣ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ሎት 8፤ የጽዳት ዕቃዎችን ሎት 9፤ የደንብ ልብስ ሎት 10 የሥራ ልብስ ስፌት ሎት 11 ፤የህንፃ ቁሳቁስ እና የቧንቧ እቃዎች ሎት 12 ፧ የቢሮ ፓርትሽን ፤ ሴኒተሪ እና የቢሮ እቃዎች ጥገና ሎት 13፤ የአይቲ ዕቃዎች ጥገና ሎት 14፤ የካፌ እና መስተንግዶ አገልግሎት ሎት 15፤ አልትራሳውንድ አገልግሎት የሚሰጥ ሎት 16፤ የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ።
1. ከሚገዛው ዕቃ አገልግሎት ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TN No/ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልፅ የምዝገባ የምስክር ወረቀት /በዌብ ሳይት የተመዘገቡ ተጫራቾች ከዌብሳይቱ ላይ ኘሪንት አድርገው ማቅረብ የሚችሉ።
3. በግዥ አዋጁ መሠረት ጥቃቅንና አነስተኛ እራሳቸው በሚያመርቱት ምርት ላይ የምናበረታታ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
4. ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ከ5ዐ ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(CPO) የሚወዳደሩበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ የሎት 1 40,000 ብር የሎት 2 30,000 ብር ሎት 3–20,000 ብር ሎት 4 30,000 ሎት 5 50,000 ብር፣ሎት 6=10,000 ብር ሎት 7–20,000 ብር ሎት፤8–20,000 ብር ሎት 9–20,000 ብር ሎት 10=5,000 ብር ሎት 11–20,000ብር ሎት 12 40,000 ብር ሎት 13 5,000ብር ሎት 14–10,000 ብር ሎት 15= 10,000 ብር ሎት 16=1,000 ብር በጤና ጣቢያው ስም በተዘጋጀ የክፍያ ትዕዛዝ |CPO/ ማስያዝ የሚገባቸው ሲሆን ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙትን CPO ዋናውን ወይም ገንዘብ ደረሰኝ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን የጨረታ- የከፈሉበትን ደረሰን ኮፒ " ማስከበሪያ ያላስያዙ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
6. ተቋማችን የሚገዛቸውን የአገልግሎት የዕቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በየሎቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 በመክፈል 4ኛ ፎቅ ከቢሮቁጥር 401 መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በአንድ ወጥ በታሸገ ኦርጅናል ፖስታ እና በታሸገ ኮፒ ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ቫትንያላካተተ፣ የድርጅቱን ህጋዊማህተም አድርጐ የማያቀርብ፤ ስርዝ ድልዝ ያደረገ እና አማራጭ ጨረታ የተጠቀሙ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።
9. የጨረታው ሣጥን በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ታሽጎ በማግስቱ በስራ ቀን ጠዋት በ3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጨረታው በግልጽ ይከፈታል።
10. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጥራት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በሚገኘው ግዥ ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸው። ናሙና ያላቀረቡ ተወዳዳሪዎች ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል። ቋሚ ዕቃዎችን እቃዎች በተመለከተ ግን ደረጃና ጥራታቸውን የሚገልፅ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሠነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይገባቸዋል።
11. የተጫራቾች አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ጤና ጣቢያ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
12. የጽሕፈት መሳሪያዎች የጽዳት እቃዎች የደንብ ልብስ እና የህንፃ ቁሳቁሶች ሳጥኑ ከመታሸጉ ከአንድ ቀን በፊት ሳምፕል እድታስገቡ ስንል እናሳውቃለን።
13. ሎት 11 ሎት 12 ሎት 13 በመስሪያ ቤቱ ውስጥ ተገኝተው እቃዎችን እና ቦታውን አይተው ሰነዱን ሞልተው ሲመልሱ ከሰነዱ ጋር እቃውን ወይም ቦታውን ለማየት ደብዳቤ አያይዘው እዲያቀርቡ።
14. መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ 20% /ሀያ ከመቶ/ ጨምሮም ቀንሶም መግዛት ይችላል።
15. የጨረታው መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- ሸጐሌ አንበሳ ጋራዥ አጠገብ ስልክ ቁጥር 011 259-2426/ 011 273 7447 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሸጎሌ ጤና ጣቢያ
