በአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ የፋ/አሰ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት በተዘረዘረው መሰረት መስፈርቱን ከምታሟሉ ተወዳዳሪዎች አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2019
በአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ የፋ/አሰ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት በፑላችን ስር ለሚገኙ ለተለያዩ ጽ/ቤቶቸ አገልገሎት የሚሰጡ አላቂ እቃዎች፣ የእንስሳት ህክምና ቀሳቁስ እና መድሀኒት፣ የህትመት ስራዎች፣ የተሸከርካሪ ኪራይ፣ የጋራጅ( ተሸከርካሪ ጥገና አገልግሎት) እንዲሁም ልዩ ልዩ አገልገሎቶችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት መስፈርቱን ከምታሟሉ ተወዳዳሪዎች አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል፡፡
1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
5. የጨረታ ሰነዱን አራት ኪሎ በሚገኘው የክ/ከተማው አስተዳደር ህንፃ በዋና ስራ አስፈጻሚ የፋ/አስ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ 9ኛ ፎቅ 902 ቁጥር ጋዜጣው ከወጣበት ቀን 2018 ዓ.ም እስከ አስረኛው የስራ ቀን 2018 ዓ.ም ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ዘውትር በስራ ቀን የማይመለስ 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በማዘጋጀት እና በማሸግ አራዳ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ የግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 11ኛው የስራ ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሸጎ በአራዳ ከፍለ ከተማ አስተዳደር በዋና ስራ አስፈፃሚ የግዥ ቡድን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች የጫረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በየዘርፉ በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ፣በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ የአጠቃላዩን ብር 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል
12. በጥቃቅን ተደራጅተው በዘርፉ ለተሰማሩ ተጫራቾች የተገለጹትን ቁሳቁሶች/እቃዎች/የአምራችነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ይህ ካልሆነ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ መግዛት እና የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የአራዳ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ የአስ/ፋ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን
