Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀላባ ዞን የአቶት ኡሎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ሀላባ ዞን ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline22 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 100/አንድ መቶ/
  • opening date በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Categories

የሃላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴ/ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የሃላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴ/ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1ኛ/ የጽ/መሣሪያ እና ሌሎች አላቂ የጽዳት ዕቃዎች (ሎት-1)

2ኛ/ የሞተር ሳይክል (ሎት-2)

3ኛ/ ኤሌክትሮኒክስ (ሎት-3)

4ኛ/ generator (ሎት 4)

5ኛ/ ፈርኒቸር (ሎት-5)

በዚህ መሠረት፡-

በዘርፉ የተሰማራችሁ የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።

የኦዲተርነት እና የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት ያላቸው።

የቫት ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ተወዳዳሪዎች የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ከሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተወዳዳሪዎች ለያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ 21 ቀናት ከፋፋይ/ንብ/አስ/የስ/ሂደት ሰነዱን ገዝተው መውሰድ ይችላሉ።

ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ለያንዳንዱ 5000 (አምስት ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዶቻቸውን እያንዳንዳቸውን አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 01 ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አለመገኘታቸው ጽ/ቤቱን ጨረታውን ከመክፈት የሚያግደው ነገር አይኖርም።

የጨረታው መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

የጨረታው አሸናፊ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ለወረዳው/ፋይ/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ +251913459200/ቁ / +251916550180 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የሃላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender