Tender Detail

Tender Details

  • Company የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ደሴ ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 033-111-7763
  • Website
  • Deadline21 Sep 2026, 9:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500 (አምስት መቶ ብር)
  • opening dateSep 21, 2026 10:00 AM
  • Categories

የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለደሴ ዙሪያ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የቢሮ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለደሴ ዙሪያ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የቢሮ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።

ሎት 1. 034 ቀበሌ አደይ ጤና ኬላ ግንባታ

ሎት 2. 034 ቀበሌ አደይ እንስሳት ክሊኒክ ግንባታ

ሎት 3. 034 ቀበሌ አደይ አስተዳደር ቢሮ ግንባታ

ሎት 4. 037 ቀበሌ ጠባሲት ጤና ኬላ ግንባታ

ሎት 5. 037 ቀበሌ እንስሳት ክሊኒክ ግንባታ

ሎት 6 038 ቀበሌ ጌልሻ አስተዳደር ግንባታ

ሎት 7 038 ቀበሌ ሸድ ግንባታ

በዚህም መሰረት

1.      ጠቅላላ ስራና ህንፃ ስራ ተቋራጭ

2.    ተጫራቾች ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ፈቃድ ያላቸው።

3.    በግንባታ ከ2018 ዓ.ም በፊት የወጣ ፈቃድ ከሆነ የመልካም ስራ አፈጻጸም መረጃ ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን አዲስ ፈቃድ ያወጡ ከሆነ ግን ማቅረብ አይጠበቅባቸውም።

4.    የቫት ተመዝጋቢ የሆነ።

5.    የዘመኑን ግብር የከፈለ።

6.    በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።

7.    የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል።

8.    ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በመለየት ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

9.    ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከወሰዱ በኋላ ዋጋውን ሞልተው ሲያስገቡ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10.   የጨረታው ሰነድ ከደሴ ዙ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።

11.    ጨረታዉ ከ26/12/2018ዓ.ም እስከ 10/01/2019 ዓ.ም ድረስ በአየር ላይ ይውላል

12.   ጨረታው በ11/1/2019 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል።

13.   ተጫራቾች ለሚሰሩበት ግንባታ ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተመሰረተ ሲፒኦ ቢድቦንድ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም የጨረታው አሸናፊ ከሆኑ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው። የውል ማስከበሪያ ካልያስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ 2% ፐርሰንቱ ይወረሳል።

14.   ተሸናፊ ተጫራቾች በመመሪያው መሰረት ያስያዙት 2% ሲፒኦ ከአምስት ቀን በኋላ ይመለስላቸዋል።

15.   አሸናፊው አካል ያሽነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያሲዝ ይሆናል።

16.   የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም የተሰረዘ ካለ ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ።

17.   ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

18.   አንድ ተጫራች ድርጅት ከአንድ በላይ መወዳደር አይችልም።

 

የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender