በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት የሚከተሉትን ግብዓቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት የሚከተሉትን ግብዓቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች
2. ሌሎች የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች
3. የፅዳት እቃዎች
4. የደንብ ልብስ
5. የህትመት ውጤቶች
ስለዚህ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ማቅረብ የሚችሉ
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
5. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ከ(egp/ www.ppa.gov.et (https://www.ppa.gov.et/)) ፕሪንት አድርገው መስፈርቶች በማሟላት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
6. ጥቃቅንና አነስተኛ ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሆኑ እሴት ጨምረው ምን ዓይነት ምርት እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ/ ጅምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራች ጋር የትስስር ሰነድ እና ውል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።ካልሆነ ግን እንደ ማንኛውም ተጫራች ሰነድ ገዝተው እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ብቻ በማስያዝ መወዳደር የሚችሉ ይሆናል።
7. ማንኛውም ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. በአንድ የዕቃ መግለጫ ዝርዝር ላይ ማቅረብ የሚቻለው 1(አንድ) ናሙና ብቻ ነው።
9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በግልፅ በመሙላት ስርዝ ድልዝ/በፍሉድ ጠፍቶ የተፃፈ ተቀባይነት የለውም። ይህም ሆኖ ሲገኝ ስርዝ ድልዝ ያለበት የዕቃ ዓይነት ከውድድር ውጪ ይሆናል። በተጨማሪ እያንዳንዱ የገዙት ሰነድ ላይ ድርጅቱን የሚገልፅ ስምና ፊርማ እና ማህተም በመምታት ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ በሁለቱም ፖስታዎች በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በፋይናንስ ፅ/ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀበት ሳጥን ውስጥ በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም በ11ኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው እለት ከረፋዱ 4፡30 ላይ ይከፈታል።
10.ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ የጨረታ ማስከበሪያ በሎቱ መሰረት የተገለፀውን የገንዘብ ዋስትና ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
v ለሎት አንድ የፅህፈት መሳሪያዎች 57,150.00 CPO ብቻ
v ለሎት ሁለት ሌሎች የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች 7830.00 CPO ብቻ
v ለሎት ሶስት የጽዳት እቃዎች 114,000.00 CPO ብቻ
v ለሎት አራት የሠራተኛ ደንብ ልብስ 155,629.00 CPO
v ለሎት አምስት የህትመት ውጤቶች 13,500.00 CPO ብቻ አስመልክቶ
11.የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናን አስመልክቶ ከላይ በተገለፀው መሰረት ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዥያ ትእዛዝ (CPO) ብቻ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል አሰርተው ማቅረብ አለባቸው።
12.አሸናፊ የሚሆኑት ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
13.ተጫራቾች የማይመለስ ብር 400.00 ብቻ በመክፈል ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘ የጨረታ ሰነድ በፋይናንስ ፅ/ቤት ቢሮ 4ኛ ፎቅ ላይ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።
14.አሸናፊ የሆነው ተጫራች በራሱ ትራንስፖርትና ወጪ ያሸነፈባቸውን እቃዎች ጥራቱ ከተረጋገጠ በኋላ ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል።
15.መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
16.ለተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 97 11 15 04/ 09 41 93 43 62 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
· አድራሻ፡- ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል በሚወስደው አስፋልት ላይ ቅሊንጦ ማረሚያ ዝቅ ብሎ ከከነማ ፋርማሲ አጠገበ ያለው ህንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ ፋይናንስ ፅ/ቤት የቢሮ ቁጥር 13 እንገኛለን።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት
