Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ክተማ ወረዳ 9 ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው ያኢጉለሌ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address , Phone: 09 13 39 78 64
  • Website
  • Deadline13 Sep 2026, 12:24 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ)
  • opening dateበአስራ አንደኛው ቀን ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Categories

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው ያኢጉለሌ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የመጀመሪያ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

መለያ ቁጥር 001/19

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው ያኢጉለሌ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሎት ቁጥር የሎት ዝርዝር ሲፒኦ ማስያዣ 1% የሎት ቁጥር የሎት ዝርዝር ሲፒኦ ማስያዣ 1%
ሎት 1 የደንብልብስ 6,000 ሎት 7 ቋሚ እቃ 7,000
ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃ 5,000 ሎት 8 ህንፃና ቁስቁስ ጥገና ለተገጣጣሚ እድሳት 4,000
ሎት 3 የህትመት ስራዎች 500 ሎት 9 ለፕላንት ማሽነሪ ጥገና 2,000
ሎት 4 የመጀመሪያ ህክምና መስጫ መድኃኒት 2,000      
ሎት 5 አላቂ የት/ት ዕቃዎች 5,000      
ሎት 6 በአላቂ የፅዳት ዕቃዎች 5,000      
  1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. በጨረታው የሚወዳደር የግዥው መጠን ከ100,000 በላይ ከሆነ የቫት ከፋይነት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  4. አነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ የራሳችሁን እሴት ያልጨመራችሁ እና አምራች ያልሆናችሁ እንደማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታ ሰነድ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መወዳደር ትችላላችሁ።
  5. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውን ከመጫረቻ ሰነድ ዋናው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ዕቃዎች ዝርዝር ከሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ያኢጉለሌ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በመምጣት በአንድ ሎት 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) የማይመለስ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ በየሎቱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሆኖ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ዋናውንና ቅጅውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ውስጥ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 (ለአስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ዋጋ በመሙላት ማስገባት አለባችሁ።
  10. በአስረኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል።
  11. መስሪያ ቤቱ በሚገዛቸው ዕቃዎች ላይ 20% የመጨመርም የመቀነስም መብት አለው።
  12. በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ቢሮ ቁ 3 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁ. 09 13 39 78 64 / 09 11 52 21 82 / 09 72 26 66 75 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  13. ናሙና መቅረብ ባለበት ዕቃዎች ላይ ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
  14. አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ያኢጉለሌ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረት ክፍል ማቅረብ አለባቸው።

ማሳሰቢያ፦ መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ መድሃኒዓለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ባለው ኮብልስቶን 30 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።

ስልክ ቁጥር፡- 09 13 39 78 64 / 09 11 55 21 82 / 09 72 26 66 75

ያኢጉለሌ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁ.3 የጨረታ ሳጥኑ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው ያኢጉለሌ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender