በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የጥበብ በቀጨኔ ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር ግልጽ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡-01/2019
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የጥብብ በቀጨኔ ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር ግልጽ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡- አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ የደንብና ስራ አልባሳት፣ የተለያዩ የህትመት አይነቶች፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እና ኮምፒውተርና የኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች እንዲሁም የላወንደሪ ማሽን እና ፍሪጅ Network Infrastructure for Eight Health centers ወይም የኔትዎርክ ዝርጋታ፤ የተለያዩ ቋሚ እቃዎችና መሳሪያዎች፤ የሰው መድሃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች የህክምና መገልገያ እቃዎች የተለያዩ የስፌትና የጥገና አገልግሎቶች እንዲሁም የካፊቴሪያ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ልታሟሉ የሚገባችሁ መስፈርቶች፡-
1. በመስኩ ህጋዊ ሰነድ የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኖራቸው በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች ሰነዶቻቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሙሉ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን መፃፍ ሲኖርባቸው በተጨማሪም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ጉ/ክ/ወ/4 ጥበብ በቀጨኔ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 37 38 ፋይናንስ ክፍል ቀርቦ በመግዛት 10ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 11፡00 ታሽጎ በ11ኛው ቀን 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል። የመክፈቻው ቀን በዓላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ በስራ ቀን ይከፈታል።
3. የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ ተመላሽ የሚሆን የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ CPO በእያንዳንዱ ሎት፡- ለሎት 1 - ለአላቂ የቢሮ ዕቃዎች ብር 10,000 ለሎት 2 - ለአላቂ የጽዳት ዕቃዎች ብር 10,000፣ ለሎት 3 - የደንብና የስራ አልባሳት ግዥ ብር 20,000፣ ለሎት 4 - ለተለያዩ የህትመት አይነቶች ብር 5,000 ፣ ለሎት 5 - ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ኮምፒውተር የኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች ብር 25,000፣ ለሎት 6-የሰው መድሃኒቶች እና የላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች ብር 10,000 ሎት 7. የህከምና መገልገያ እቃዎች ብር 10,000 ለሎት 8. የተለያዩ ቋሚ የፈርኒቸር እቃዎች ብር 10,000 ለሎት 9. Network lnfrastucture for Eight Health centers)ወይም የኔትወረክ ዝርጋታ እቃዎችን ጨምሮ ብር 30,000 ለሎት 10. የደንብ ልብስ የስፌት አገልግሎት ብር 5000 ሎት 11. የኤሌክትሪክ እና ህንፃ መሣሪያ ብር 5000 / ሎት 12. የካፍቴሪያ አገልግሎት ብር 30,000 በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። በመሆኑም የጨረታ ሰነዱን በሎት የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ/ ብር መግዛት እና መጫረት ትችላላችሁ።
4. የተጠየቁ ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ትክክለኛ ናሙና ወይም ስፔስፍኬሽን (Specification)፣ ፎቶ ግራፍ፣ ካታሎግ ወይም ማንዋል ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ናሙና ተጠይቀው ባላቀረባችሁባቸው ላይ መጫረት አይቻልም።
5. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከታወቀበት ከ8ኛው ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ጥ/በቀ/ጤ/ጣ ቢሮ ቁጥር 38 በግንባር በመቅረብ ወይም የድርጅቱን ውክልና እና መታወቂያ በያዘ ግለሰብ ውል መዋዋል ሲኖርባቸው ይህ ሆኖ ባይገኝ ግን የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ በማድረግ መ/ቤቱ የተሻለውን አማራጭ ይወስዳል።
6. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ዕቃ ትክክለኛውን ብራንድ(ዓይነት) ናሙና እና የዕቃ መግለጫ (Specification)፣ ካታሎግ ወይም ማንዋል፣ የእቃው ፎት ግራፍ ማቅረብ ሲኖርባቸው ጨረታው ጥራትን እና ዋጋን መነሻ አድርጎ ውሳኔ ይሰጣል።
7. ተጫራቾች ንብረቱን በራሳቸው ትራንስፖርት እና የጉልበት ዋጋ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 43 ድረስ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% (CPO)፣ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ባይሆን ግን በጨረታ የተያዘው CPO በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛል።
9. መ/ቤቱ በጨረታ ላይ ከተጠቀሱት እቃዎች ብዛት ላይ 20% ቀንሶ ወይም 20% ጨምሮ ከአሸናፊ ድርጅት የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
10.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽይከፈታል፡፡ ካልተገኙም ጨረታው ከመከፈት አይደናቀፍም። አድራሻችን፡-ጉ/ክ/ከ/ወረዳ 4 ጥበብ በቀጨኔ ጤና ጣቢያ ልዩ ስሙ ከቀጨኔ መድኃኒአለም ቤተ ክርስቲያን በ1 ኛው መንገድ ከቤተ ክርስቲያኑ 400 ሜትር ከፍ ብሎ።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ጥበብ በቀጨኔ ጤና ጣቢያ በግንባር በመቅረብ ወይም ስልክ ቁጥር 011 111-1409 / 011 111-1886, ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የጥብብ በቀጨኔ ጤና ጣቢያ
