በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ገሊላ ቅድመ አንደኛ እና የመ/ደ/ት/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት፡-
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ገሊላ ቅድመ አንደኛ ፤አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ገሊላ ቅድመ አንደኛ እና የመ/ደ/ት/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት፡-
ሎት 1 የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ስፌት (የበጀት ርዕስ 6211) 1,100,000×2%= 22000
ሎት 2 አላቂ የቢሮ መሳሪያዎች (የበጀት ርዕስ 6212) 820,000×2%= 16400
ሎት 3 የሠራተኞች መታወቂያና ባጅ “የተማሪ መታወቂያና ባነር( የበጀት ርዕስ 6213)-120,000×2%=2400
ሎት 4 አላቂ የህክምና ዕቃዎች(የበጀት ርዕስ 6214) -30,0002% 600
ሎት 5 አላቂ የትምህርት መሳሪያዎች (የበጀት ርዕስ 6215) 200,000×2%=4000
ሎት 6 አላቂ የፅዳት መሳሪያዎች (የበጀት ርዕስ 6218) –1,000,000×2%=20,000
ሎት 7 ቋሚ አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች( (የበጀት ርዕስ 6219) -200,000×2%=4000
ሎት 8 የፕላን ማሽነሪ እድሳትና ጥገና (የበጀት ዕርስ 6243) - 100,000×2%=2000
ሎት 9 ቋሚ ዕቃ( ፕላንት ማሽነሪ) የበጀት ርዕስ 6313 ) -1,650,000×2%=33,000
ሎት 10 . ልዩ ልዩ ( ውሃ ቆሎ ኩኪስ) የበጀት ርዕስ 6419) 200,000×2% 4000
ሎት11. ለመስተንግዶ የሰራተኛ እና የመምህራን የት/ቤቱ የሻይ ክበብ(6233) 900,000×2%=18,000
በየ ሎቱ የተዘረዘረው የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ድምር ብር 131,800
ከላይ የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የብርህንና ሰላም የተረጋገጠ QR ደረሰኝ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. በገንዘብ ሚኒስቴር በእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር በተበጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም በ2019 ዓ.ም በጨረታዉ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸዉን ከሚመለከተዉ ግብር ሰብሳቢ አካል የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ድጋፍ የሚደረገዉ የምታመርቱት ምርት ላይ ብቻ ነው።
4. የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በት /ቤቱ የክፍያና ሂሳብ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
5. የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባችሁ።
6. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የዕቃውን 10% (ፕርሰንት) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝና ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚ መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. የሚጫረቱባቸውን እቃዎች ለመለየት የሚያስችል ሳምፕል አላቂ እቃዎች ናሙና የተሟላ ቋሚ ዕቃዎችን ኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸር ዕቃዎችን በፎቶ የተደገፈ እስፔስፊኬሽን ከመከፈቱ ከሁለት ቀን በፊት ከመወዳደሪው ጨረታ ሰነዳቸው ጋር ተያይዘወው ማቅረብ አለባቸው።
8. የሚያቀርቡት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በማቅረብ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት እስከ 10 ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ የክፍያና ሂሳብ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ በስራ ሰዓት ለዚህ ጨረታ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
9. የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያው በወጣ 10ኛ ቀን ከቀኑ 11፡30 ያበቃና በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል። እለቱ የዝግ ቀን ከሆነ የሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ይከፈታል።
10. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለዉ።
11. የጨረታው ዋጋ ቫትን አካቶ በግልጽ መቀመጥ ይኖርበታል።
12. የጨረታ ሰነዱ ማህተም እና ፊርማ ተደርጎ ተመላሽ መሆን አለበት ሰነዱን ያልመለሰ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።
13. አድራሻ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ከሰባተኛ ወደ አብነት በሚወስደው መንገድ በቀድሞ ወረዳ 2 ዝቅ ብሎ ባለው አስፋልት 500 /አምስት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ዘውዴ ቢራቱ መንገድ ከመተተባበር ት/ቤት ዝቅ ብሎ
ስልክ 011-278 7603/02 011-229 3116
ገሊላ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
