በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በምዕ/ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ወረዳ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በምዕ/ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ወረዳ ቀረርየመንግስት ደን ውስጥ 2973.32 ሜ/ኩብ ቀይ ባህርዛፍ ቁም ደን ፣ በደ/ወሎ ዞን ደሴ ዙሪያ እና ተሁለደሬ ወረዳዎች በተለያዩ ቀበሌዎች በተለያዩ የመንግስት ደኖች ውስጥ 10,858.02 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ፣5.5 ሜ/ኩብ ነጭ ባህርዛፍ ቁም ዴን እና የወደቀና የደረቀ የፈ/ጽድ 322.98 ሜ/ኩብ በድምሩ 11,1865 ሜ/ኩብ ፣ ደ/ጎንደር ዞን ገና በጌምድር፣ላ/ጋይንት እና ደራ ወረዳዎች በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ የመንግስት ደኖች ውስጥ 4047.7 ሜ/ኩብ የፈ/ፅድ፣ 23,870.16 ሜ/ኩብ ነጭ ባህር ዛፍ እና 60.83 ሜ/ኩብ ቀይ ባህርዛፍ ቁም ደን በድምሩ 27,978.69 ሜ/ኩብ ቁም ደን፣ በሰ/ሽዋ ዞን ባሶና ወረና ወረዳ ጎሺ : አገር : ቀበሌ አባሲ አገር የመንግስት ደን እና ጣርማ በር ወረዳ ደብርማዕዛ ቀበሌ ደብረ ማዕዛ የመንግስት ደን ውስጥ የሚገኘውን 20,630,46 ሜ/ኩብ የነጭባህርዛፍ ፣465.59 ሜ/ኩብ የፈ/ፅድ እና 2998.85 ሜ/ኩብ ፓይነስ ፓቹላ ቁም ደን በድምሩ 24,094,9 ሜ/ኩብ ቁም ደን ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. የሽያጩ መጠን 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ /ብር በላይ ከሆነ የተእታ VAT ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ለጨረታ የቀረበውን ቁም ደን /ምርቶች ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ስዓት በቦታው ተገኝተው ማየት ይችላሉ።
4. የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ዉስጥ/ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ/ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕርዳር ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ማዳቀያ ግቢ ዉስጥ
1. ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 06 እና በሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች የማይመለስ 200 (ሁለትመቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (Bid Bond) በባንክ የተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ /CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቶች መግዛት የሚፈልጉትን ቁም ደን ምርቶች/ በአሪጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ስምና አድራሻቸዉን በመፃፍ ፈርመው በመሙያው ሰነዱ ላይ ማህተም በማስቀመጥ የታሸገውን የጨረታ ፖስታ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06፣ደ/ብርሃንና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች «የቁም ደን ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ›› ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ (ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ) እስከ መጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን በ4፡ ዐዐ ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጅ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል፡፡
7. ተጫራቾች የሚሞሉት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተእታን አይጨምርም፡፡ ሆኖም አሸናፊዉ ባሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል፡፡
8. ተጫራቾች ቁም ደኑን በተመለከተ ቅልቅል ደን ተብሎ የቀረበውን ሁሉንም ክፍልፋይመሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
9. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ::
10. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
11. ለተጨማሪ መረጃ፡-
☞ በስልክ ቁጥር ባ/ዳር 0582263095፣ደ/ታቦር 0584410306፤ደ/ብርሃን 0116375017፣
እንጅባራ 0582270485 ደ/ማርቆስ 0588719004/ 0914716636 -
→ መጠየቅ ይችላል፡፡
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት
