በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የም/ባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በዞኑ ስር ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በ2019 ዓ.ም በጀት የመጀመሪያ ዙር ግዥ፣
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የም/ባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በዞኑ ስር ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በ2019 ዓ.ም በጀት የመጀመሪያ ዙር ግዥ፣
- የደንብ ልብስ ጫማ እና የስፌት አገልግሎት
- የፅህፈት መሳሪያ፣
- የምግብ እቃ፣
- አላቂ የብሮ እቃዎች
- የግንባታ እቃዎች
- የመኪና ጎማ እና ባትሪ፤
- ቋሚ እቃ (ፈርኒቸርና ኤሌክትሮኒክስ)፤
- የሞተር ሳይክሎች 150 cc እና ከዛ በታች፤
- የቢሮ ውስጥ ምንጣፎችና ማስዋቢያ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የመወዳደሪያ መስፈርት
- የንግድ ምዝገባ ቁጥር ያለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የ2018 ግብርን ከፍሎ ያጠናቀቀ፡፡ የንግድ ፍቃዱን ለ 2019 የስራ ዘመን ያሳደሰ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ከግብር ከፍያ ነፃ ስለመሆኑ ማስረጃ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው የቫት ተመዝጋቢ የሆነ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር በምስራቅ ባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ስም አሰርተው በእጃቸው ይዘው መቅረብ ሲኖርባቸው ከ (2 አመት) ወዲህ አዲስ የተደራጁ ማ/ራት ካደራጃቸው አካል የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና ደብዳቤ በእጃቸው ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተደራጁ ማህበራት ካደራጃቸው አካል ህጋዊ መሀበር መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
- ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በህትመት (ሃርድ ኮፒ) ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ከምስራቅ ባሌ ዞን ገቢዎች መስሪያ ቤት የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል መግዛት ይችላል፡፡
- ጨረታውን ተወዳድሮ ያሸነፈው የሚፈርመው ውል ለግማሽ አመት ወይም ለ 6 ወር እንደሚቆይ ማወቅ ሲኖርበት፤ይህንን አውቆ ውል ለመግባት ፍቃደኛ የሆነ፡፡
- ጨረታውን ተወዳድሮ ያሸነፈው ተጫራች የውል ማስከበሪያ ከተሰጠው ትእዛዝ ውስጥ 10% CPO ለማስያዝ ፍቃደኛ የሆነ:
- የተለያዩ ተቀናናሽ ከፍያዎችን ማለትም የቲኦቲ እና ከቫት 15 % ግማሹን (7.5) ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ::
- ተጫራች ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለፀ እና ትእዛዝ ከተቀበለ በኋላ ባሉት በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ የወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቀናት ውስጥ ምስራቅ ባሌ ዞን ገንዝብ ጽ/ ቤት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተወዳዳሪዎች ለውድድር ሲቀርቡ ቴክኒካል ማስረጃቸውን ዋናውንና፤ኮፒውን ለየብቻ በሰም አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራች ፋይናንሺያል ማስረጃ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በሰም በማሸግ ሙሉ ሰነዱን፤የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በጥንቃቄ በግልፅ በማስቀመጥ፤ ስም፣ ፊርማ፣ የስልክ ቁጥራቸውን ፣ የድርጅታቸውን አድራሻ ፣ ማህተም ፣ በመሙላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ማቅረቢያ ጊዜ የሚያበቃው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ 11ኛ (አስራ አንደኛው) የስራ ቀን ከጠዋቱ 3.00 ሲሆን፤ ጨረታው የሚከፈተው በዚያው ቀን ከጠዋቱ 3.30 ተወዳዳሪዎች/ህጋዊ ወኪሎች የግዥ ኮሚቴዎች፣ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ባሉበት በምስራቅ ባሌዞን ገንዘብ ጽ/ቤት፣ በግገርከፍል ቁጥር 8 ውስጥ በግልጽ ይሆናል:
- የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ባጋጣሚ የስራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ ዘግይቶ የሚቀርብ ማንኛውም የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤ የዋጋ ማሻሻል አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች መጫረት የሚችሉት ባላቸው የንግድ ፍቃድ ዘርፍ ብቻ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ከንግድ ፍቃዳቸው ዘርፍ ውጭ መወዳደር አይችሉም፡፡
- ገዥው መስሪያ ቤት የግዥውን መጠን በ20 ፐርሰንት ቀንሶ ወይም ጨምሮ ሊገዛ ይችላል፡፡
- ገዥው መስሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የእቃ ሞዴል የመሙላት ግዴታ አለባቸው የሚያቀርቡትን እቃ ሞዴል ካልሞሉ ዋጋቸው ተቀባይነት አይኖረውም::
- አቅራቢዎች ሚገጣጠሙ የሚታሰሩ ንብረቶችን (ወንበሮች፡ሼልፎች ጠረጴዛዎች) አስተካክለው ገጥመው ለንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የላፕቶፕ ኮምፒውተር ፡አሸናፊ ተወዳዳሪ ለı ወር የሚቆይ የዋስትና ጊዜ መኖሩን አውቆ መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡ እቃው ቸግር ካለበት የመመለስ ግዴታ አለባቸው የውል ማስከበሪያቸውም የዋስትና ጊዜው ሲያበቃ የሚመለስ መሆኑን መገንዘብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ
- ተጫራች ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎችን ከጨረታ ሰነድ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ::
- ለአቅራቢው ከፍያ የሚፈጸመው በውድድሩ መሰረት ጥራት ያለውን እቃ በተፈለገው ጊዜ፤መጠን፤ቦታ፤ አይነት ሲያቀርብ በግዥ ኮሚቴዎች /በሚመለከታቸው ባለሙያ አካላት ታይቶ ርከከብ ከተደረገና ህጋዊ ደረሰኝ ከተቆረጠ ቦኋላ ይሆናል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910373081/0913810062/0917557727/0975896720::
የምስራቅ ባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት፣ ጊኒር
