የኮምቦልቻ ዶሮ ሀብት ልማት ኢንተርፕራይዝ የ2019 በጀት የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኮምቦልቻ ዶሮ ሀብት ልማት ኢንተርፕራይዝ የ2019 በጀት ዓመት የዶሮ መኖ ጥሬ እቃዎች ፤ የተመጣጠነ የተዘጋጀ የዶሮ መኖ ጥሬ እቃዎች ፤ የጽህፈት መሳሪያዎች እና የጽዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የቧንቧ እቃዎች፣ የኢንኩቤተር ማሸን መለዋወጫ እቃዎች፣ የዶሮ እርባታ እቃዎች፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ፤ መድሀኒቶች፣ ክትባቶች እና ቫይታሚኖች እና የማዳበሪያ ከረጢት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን።
1. በዘመኑ የታደሰ በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው
4. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የድርጅቱን ስም አድራሻ ማሕተም ፊርማ በማድረግ በሚነበብ መልኩ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ማቅረብ የሚችል፣
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ / በመክፈል ከመ/ቤታችን ፕሮሞሽንና እና ገበያ ልማት ደጋፊ የስራ ሂደት ሽያጭ ክፍል ማግኘት ይቻላል፣
6. የተመጣጠነ የተዘጋጀ የዶሮ መኖ ጥሬ እቃ የብቃት እና የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት ኦርጅናሉን በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊማህተም በማድረግ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከቀን 26/12/208 እስከ ቀን 2/13/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፣
8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም በቀን 2/13/2018 ዓ. ም4፡30 ይከፈታል
9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግም ሆነ ራሳቸውን ማግለል እንደማይቻል።
10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የዋጋውን 1/አንድ/ ከመቶ በጥሬ ገንዘብም ሆነ በሲፒኦ ማሰያዝ ይኖርበታል።
11. የእቃው ርክክብ በተመለከተ ኮምቦልቻ ዶሮ ሃብት ልማት ኢንተርፕራይዝ ግቢ ድረስ ማስረከብ የሚችል፤
12. ጨረታውን ተወዳድሮ ከሚያሸንፍ አቅራቢ እስከ 50 በመቶ ተጨማሪ ማዘዝም ሆነ ቀንሶ መግዛት ይቻላል
13. የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ5 ተከታታይ የሰራ ቀናት ውስጥ የዋጋውን የውል ማስከበሪያ 10‰ ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ አሰይዞ ውል መግባት ይኖርበታል፡፡ ካልሆነ ጨረታውን ለመሳተፍ ያስያዘው ከመቶ ገንዘብ የሚወረስ ይሆናል፤
14. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
ለበለጠ መረጃ 033 351 0660
የኮምቦልቻ ዶሮ ሀብት ልማት ኢንተርፕራይዝ
