በኮ/ቀ/ ኪ/ ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019
በኮ/ቀ/ ኪ/ ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1. የደንብ ልብስ
- ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3. የህትመት ስራ
- ሎት 4. የህክምና እቃዎች
- ሎት 5. አላቂ የትምህርት እቃዎች
- ሎት 6. የጽዳት እቃዎች
- ሎት 7. የት/ት መሳሪያዎች (መጽሀፍት) መግዣ
- ሎት 8. ፕላት ማሸነሪ
- ሎት 9. የተገጣጣሚ እና ቁሳቁስ መግዣ
- ሎት 10. ኤሌክትሮኒከስ ጥገና
- ሎት 11. የተገጣጣሚ እና ቁሳቁስ ጥገና
- ሎት 13. የጉልበት እና የትራንስፖርት
- ሎት 15. ልዩ ልዩ ክፍያዎች
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቶች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች ከስራው ዘርፍ ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው የዘመኑ ግብር መከፈላቸውን የሚገልጽ ወቅታዊ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ት/ቤቱ በሚሸጠው ሰነድ ላይ የሚፈለግባችሁን በመሙላት እና በፖስታ በማሸግ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ በኮ/ቀ/ከ/ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት በየሎቱ የማይመለስ 200 ብር /መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዎች ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ የብር መጠን በየሎት ለእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ አለባቸው፡፡
| ሎት 1. | 21,000 |
| ሎት 2. | 25,000 |
| ሎት 3. | 2,000 |
| ሎት 4. | 1,000 |
| ሎት 5. | 17,000 |
| ሎት 6. | 20,000 |
| ሎት 7. | 15,000 |
| ሎት 8. | 15,000 |
| ሎት 9. | 15,000 |
| ሎት 10. | 1,500 |
| ሎት 11. | 10,000 |
| ሎት 13. | 6,000 |
| ሎት 15. | 3,000 |
- በጥቃቅን አነስተኛ ተቋማት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጨረታ ማስከበሪያ በውል ማስከበሪያ እና በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ምትክ ካደራጀው ተቋም በኃላፊ ብቻ የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ሲኖረው በስራ ሂደት የሚፈረም ደብዳቤ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበት የእቃ ናሙና በተመረጡ ሎት እና ሌሎች ናሙና ማቅረቢያ ዘዴ ማቅረብ አለበት፡፡
- የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና የቁሳቁስ ጥገና ላይ አሸናፊ የሚሆኑት ውላችን የአንድ ዓመት መሆኑ ይታወቅ፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በግዥ ክፍል ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና አክራሪ የበዓላት ቀን የሚውል ከሆነ ቀኑን አሳልፈን የምንከፍት መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡
- መስ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል /በሙሉ/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፦ ካራ ቆሬ ወደ ረጲ መደሃኒያለም ቤተክርስቲያን መሄጃ ፖሊስ ጣቢያውን አለፍ ብሎ የሚገኘው ት/ቤት
ተጨማሪ መረጃ፡- 0113695428 / 0113695841/
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አስተዳደር ህንጻ 1ኛ ወለል ግዥ ቢሮ ቁጥር 9፡፡
በኮ/ቀ/ ክ/ ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
