የምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2019 ዓ/ም የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን አላቂ፣ ቋሚ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች እና የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለዞኑ ሴክቴር መ/ቤት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2019 ዓ/ም የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን አላቂ፣ ቋሚ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች እና የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለዞኑ ሴክቴር መ/ቤት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ እና በተወዳዳሪዎች መመሪያ ደንብ መሠረት ተጫራቾች ቀርበው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
1. ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ማቅረብ የሚችሉና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው;
2. በመንግስት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ የምስከር ወረቀት አግባብ ካለው ህጋዊ አካል ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የ2018/2019 ዓ/ም ግብር አጠናቀው የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡና ለታከስ ከፋይነት (TIN) የተመዘገቡና ተጨማሪ ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
4. ለጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት ዋጋ 2% በተረጋገጠ (CPO) ከማስረጃቸው ጋርአያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤
5. ተጨራቶች የጨረታ ሰነዳቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር( 500) አምሰት መቶ በመከፈል የግዥ ክፍል ከመ/ቤቱ (G+1) ምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ፅ/ቤት መግዛት ይችላሉ፤
6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን ምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ፅ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዕቃ ዓይነት የቢሮ ዕቃ መሆኑን እንደዚሁም የድርጅቱን ስም በሚያቀርቡት የተለያየ ፖስታ ላይ በአሪጅናሉና በኮፒው ላይ በግልጽ በመጻፍ በድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ አስደግፈው ማቅረብ አለባቸው፤
8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ በኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
9. ተወዳዳሪዎች ናሙና እንዲቀርብባቸው የተጠየቁትን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ማቅረብና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ቆጥሮ ማስረከብ አለባቸው:
10. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአሠራ ስድስተኛው የስራ ቀን፣ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 (በስምንት ሰዓት ተኩል) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
11. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሲሆኑ ዕቃዎቹን በራሳቸው ማጓጓዣ እስከ ገዥው ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው!
12. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር 0577712547 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታንው በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የምዕራብ ወስጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት
