በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ለ2019 በጀት ዓመት የተማሪዎች ምግብ ቤት የሚውል የተለያዩ የምግብ ጥሬ ዕቃዎች የወጣ ግልፅ ጨረታ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ቢሾፍቱ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/ህ/ግ/ኮ 001/2019
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ለ2019 በጀት ዓመት የተማሪዎች ምግብ ቤት የሚውል የተለያዩ የምግብ ጥሬ ዕቃዎች የወጣ ግልፅ ጨረታ ነው፡፡
ስለሆነም፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ግብር የመከፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የታከስ ከፋይ (Tin No) የምስከር ወረቀት ፤ የአቅራቢዎች ምዝገባ/suppiler list እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 213,150.00 / ሁለት መቶ አስራ ሶስት ሺህ አንድ መቶ ሀምሳ ብር/በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) /የባንክ ዋስትና ደብዳቤ/ ቼከ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ግዥ ከፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘውን ሰነድ አንድ ቴክኒካል ኦሪጂናልና አንድ ቴከኒካል ኮፒ እና አንድ ፋይናንሽያል ኦርጅናልና አንድ ፋይናንሽያል ኮፒ በእናት ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 7፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኮሌጁ ግዥ ከፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ7፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡00 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፡፡ የመከፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው መዝጊያ ሰዓት ታሽጎ በግልጽ ይከፈታል፡፡
7. በጨረታ መክፈቻ ቀኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይስተጓጎልም፡፡
8. ተጫራቾች የአሸነፏቸውን አቅርቦቶች በሚሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንሰሳት ሕከምና እና ግብርና ኮሌጅ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል::
9. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የእንሰሳት ሕከምና እና ግብርና ኮሌጅ
ስልክ ቁጥር -0114338557 / 0912065392
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሴጅ
