Tender Detail

Tender Details

  • Company Development Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ልማት ባንክ)
  • Address ካዛንቺስ ሾንጌ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115 57 80 88
  • Websitehttps://dbe.com.et/
  • Deadline06 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityየሚጫረቱትን ንብረት መነሻ ዋጋ 10 በመቶ
  • opening date2026-08-06 10:00:00
  • Categories Office Supplies And Services , Generators , Machinery , Vehicle

የኢትዮጵይ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን አዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘረውን ንብረት በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

Development Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ልማት ባንክ)


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵይ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን አዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘረውን ንብረት በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የቀድሞ ተበዳሪው/ የመያዣ ሰጪው ስም

የንብረቶቹ ዓይነት በጥቅል

የማሽነሪ ስም

የጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር)

ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ

የጨረታ ሁኔታ

ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

1

 

ኤምቴኬ ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ

ማሽነሪዎች እና እኩፕመንት

የእንጨት ስራ ማሽነሪ (Surface planner mic, Circular saw m/c, Edge bending mic. Copy lathe m/c, Combined surface or thickness planner m/c

ብር 6,185,295.80 (ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና አምስት ብር ከሰማንያ ሳንቲም)

 

 

 

 

 

 

ገላን ከተማ ኤም ቴኬ ኢንጅነሪንግ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ

 

 

 

 

 

 

ድርድር

 

 

 

 

 

 

ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት

2

የብረት ሥራ ማሽነሪ  (lathe m/c, universal milling m/c, press brake m/c, scroll bending m/c, hydraulic bending m/c, motor unit,tube drilling m/c etc)

 

ብር 26,174,644.44 (ሃያ ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አራት ብር ከአርባ አራት ሳንቲም)

3

ዎርክ ሾፕ ዩትልትስ (Air compressor, hand pallet, liquid thank)

ብር 523,134 (አምስት መቶ ሃያ ሦስት ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ አራት ብር)

4

ስቶን ዎርክ ዩትልትስ (Special shaped stone polishing, multi-blade bridge block cutter m/c stone surface thickness calibrating m/c etc)

ብር 1,701,600.00 (አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ብር )

5

የቢሮ ዕቃዎች

ብር 650,051 (ስድስት መቶ ሃምሳ ሺህ ሃምሳ አንድ ብር)

6

ጀነሬተር

ብር 697,151 (ስድስት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ አንድ ብር)

7

ካርጎ ትራክ

3-01-77197 አአ

ብር 410,562.00 (አራት መቶ አስር ሺህ አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ብር )

 

ማሳሰቢያ፡-

1.     ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፤ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁስተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ:: ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።

2.     ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.አ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::

3.     አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል::

4.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ታወር ሁለት 5ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል:: ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ወክሎ በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ/መተዳደሪያ ደንብ ከእነ ማሻሻያዎቹ (ካለ)፤ የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፈቃድ፣ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል::

5.     15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል::

6.     አንዳንድ ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆነ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም የሚፈለገውን ቀረጥ/ታክስ ለመንግስት ለመክፈል ይገደዳል::

7.     ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ይሆናል::

8.     የንብረቱ ስሙ ንብረት ለገዥው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል:: ገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈጽማል::

9.     የጨረታ አሸናፊው ማሽነሪዎችን ለመንቀልና ለማጓጓዝ የሚያስፈልግ ወጪ በራሱ ይሸፍናል::

10. ንብረቶቹ ለጨረታ የቀረቡት በየተራ ቁጥሩ በተናጠል ነው::

11. በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የአንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክትስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524-53-73/011-524-42-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል::

12. ተጫራቾች አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ንብረቶቹን መጎብኘት ይችላሉ::

13. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

Save Tender