Tender Detail

Tender Details

  • Company Andinet Education & Training PLC
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline29 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-16 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Catering And Cafeteria Services

አንድነት ትምህርት እና ስልጠና አ.ማ. ፍላጎት ያላቸው እና ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው አገልግሎት ሰጪዎች ለካፊቴሪያ አገልግሎት በኮትራት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። አገልግሎቱ ቁርስ፣ ምሳ፣ ለስላሳ መጠጦች፣ ሻይ እና ቡና አቅርቦትን ለኩባንያው ሰራተኞችና ለተማሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብን ያካትታል።

Andinet Education & Training PLC


አንድነት ትምህርት እና ስልጠና አ.ማ.

ለጨረታ ማስታወቂያ፡ የካፌቴሪያ አገልግሎት አቅርቦት

የማስታወቂያ ቀን፡ ሐምሌ10/2017

ርዕሰ ጉዳይ፡- የካፌቴሪያ አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ

 

የጨረታ ዝርዝሮች፡–

  • ዓላማው፡– የካፊቴሪያ አገልግሎቶችን ለውጭ አገልግሎት አቅራቢ መስጠት።
  • ወርሃዊ የኪራይ መነሻ ዋጋ (መሰረታዊ አቅርቦት)፡– 20,000.00 ብር (ሃያ ሺህ ብር)
  • ብቁነት፡ በምግብና መጠጥ ወይም በመመገቢያ አገልግሎት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው አገልግሎት ሰጪዎች እና አስፈላጊ የግአት እቃዎችን በራሱ ሟሟላት የሚችል።
  • የጨረታ ሰነድ ግዥ ዋጋ 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር)
  • ሰነድ ማሰባሰብ፡– ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
  • ጨረታው የሚዘጋበት ቀን፡– ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) የስራ ቀናት።

መስፈርቶች፡

  • የታደሰ የንግድ ፈቃዳቸውን ቅጂ ያቅርቡ።
  • በተመሳሳይ ካፊቴሪያ ወይም የምግብ አገልግሎት ስራዎች ልምድ ያላቸውን ዝርዝሮች ያቅርቡ።
  • ወርሃዊ የኪራይ አቅርቦትን እና ለምግብ እና መጠጦች የእቃ ዋጋን ጨምሮ የፋይናንስ ፕሮፖዛል ያቅርቡ።

የተጠናቀቁትን የጨረታ ዶክመንቶች በታሸገ ኤንቨሎፕ የመጨረሻ ቀን ከመድረሱ በፊት ማስገባት አለባቸው። ዘግይተው ማስረከብ አይታሰብም።

N.B.፡

ተጫራቾች በራሳቸው ዲዛይን ላይ ተመስርተው በካፊቴሪያው ውስጥ ማሻሻያ ወይም እድሳት ማድረግ ከፈለገ ከኩባንያው ቀድመው ሲፈቀድ ብቻ ይፈቀድላቸዋል። ከእንደዚህ ዓይነት ማሻሻያ ጋር የተያያዙ ወጪዎች በሙሉ በጨረታ አሸናፊው ይሸፈናሉ፡፡

ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውሉ የመገልገያ እቃዎች ጨረታውን የሚያሸንፍ አካል ያሟላል፡፡

ለበለጠ መረጃ፣ አንድነት ትምህርት እና ስልጠና አ.ማ.ግዥ እና ንብረት ክፍልን በስልክ ቁጥር 0116 47 99 96/97 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

አንድነት ትምህርት እና ስልጠና አ.ማ. የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Save Tender