በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የቤት የሐራጁ ሽያጭ አዉጥቶኡል።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመበት አቶ ዳዊት ፀጋዬ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አቶ በሱፍቃድ ካሣሁን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/158745 በቀን 30/8/2016 ዓ.ም በፌ/ጠ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.280523 በቀን 15/9/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በለሚ ኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 10 በካርታ ቁጥር ቦሌ 10/19/8/6/21556/219333/02 በአቶ በሱፍቃድ ካሳሁን ስም የተመዘገበ የይዞታ ስፋት 339 ካ.ሜ የሆነው ቤት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 10,632,289 (አስር ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺ ሁለት መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሽናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት/ስም C. P.O አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሽጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሱ መሆኑን እንገልጻስን፡፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
