በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ የሰንዳፋ ሶላር ፋብሪካ የአጥር ግንባታ በኤጋ ቆርቆሮ ግዥ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለማግኘት ይፈልጋል።
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ
ብሄራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ የሰንዳፋ ሶላር ፋብሪካ የአጥር ግንባታ በኤጋ ቆርቆሮ ግዥ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለማግኘት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትጫረቱ ተጋብዛችኋል።
1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት
4. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin) ማስረጃ ማቅረብ አለበት
5. ተጫራቾች በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስም ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ ብር) በብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለየብቻው ከሰነድ ጋር በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርበታል።
6. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መሙላትና በማህተም ማረጋገጥ አለበት።
7. ተጫራች የሚያቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት።
8. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢከፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ አንደኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን በሶፍት ኮፒ መግዛት ይችላሉ
9. ተጫራቾች በገዙትና በሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፁትን ሁኔታዎች በአግባቡ በመጠቀም የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. ተጫራቾች የጨረታ የሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ 2ኛ ፎቅ ላይለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
11. ተጫራች ለጨረታ ሰነዱ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዱን ለየብቻ ለይቶ ማቅረብ ይኖርበታል።
12. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
13. አግባብነት ያለው የሙያ ብቃት ለጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 5 GC - 5) በላይ ወይም ለህንጻ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 4(BC - 4) በላይ መሆን አለባቸው ለዚህም ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት አስፈላጊ ነው።
14. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይዘጋል። በዚሁ ዕለትም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3ኛ ፎቅ ላይ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
15. ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 60 (ስልሳ) ተከታታይ ቀናት ስለሆነ ተጫራቾችም ይህንኑ አውቀው ስለመቀበላቸው በሰነዳቸው ላይ ማረጋገጥ አለባቸው።
16. ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም። ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ ለቡ መብራት ኃይል ከጀነራል መርከንታይል አጠገብ
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥራችን ስልክ: +251 924955389፣ +251 910162733 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ
