Tender Detail

Tender Details

  • Company Dire Dawa Administration Police Commission (የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን)
  • Address ድሬዳዋ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +25101117455
  • Website
  • Deadline30 May 2026, 9:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityየሚጫረቱበትን እቃ ዋጋ ብር 150,000.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/
  • opening date2026-05-30 09:30:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Cloth And Shoes

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ለ2018 በጀት ዓመት ለሰራዊቱ አገልግሎት የሚውል ቦት ጫማ የወንዶች እና ጉርድ ጫማ እንዲሁም የሴቶች ጉርድ ጫማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Dire Dawa Administration Police Commission (የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን)


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ለ2018 በጀት ዓመት ለሰራዊቱ አገልግሎት የሚውል ቦት ጫማ የወንዶች እና ጉርድ ጫማ እንዲሁም የሴቶች ጉርድ ጫማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1.     የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

2.     ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፋይ የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3.     ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆንና የጨረታው ውጤት እንደታወቀ የማይመለስ የሚጫረቱበትን እቃ ዋጋ ብር 150,000.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4.     በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ተመራጭነት አለው፡፡

5.     የቴክኒካል ሰነድ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለየብቻ በማሸግ በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6.     የጨረታ ሰነድ 7/9/2018 ቀን እስከ 21/9/18 ዓ.ም. ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን በፋይናንስና ግዢ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡

7.     ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 22/9/2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሣጥኑ ታሽጎ 3፡30 ሠዓት ይከፈታል፡፡

8.     ፖሊስ ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር 0251-11-74-55/0251-11-37-43 በመደወል ፖ.ሣ.ቁጥር 1453 መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት

Save Tender