Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
  • Address ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ጎን 200 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114709095
  • Websitehttps://ethioagri.com/
  • Deadline15 May 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-05-15 00:00:00
  • Categories Hand Tools And Workshop Equipment , Vehicle Spare Parts

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የዎርክ ሾፕ መሣሪያዎች እና የተለያዩ መኪናዎች መለዋወጫ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል

Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)


የጨረታ ማስታወቂያ



ከታች ቀጥሎ በሎት አንድ እና በሎት ሁለት የተዘረዘሩትን የዎርክ ሾፕ መሣሪያዎች እና የተለያዩ መኪናዎች መለዋወጫ እቃዎችን ለመግዛት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ./ብግጨ/12/2018

ተ.ቁ

የሎት ቁጥር

የጨረታ አይነት

የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ (የማይመለስ) ብር

የጨረታ ማስከበሪያ በብር

የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀንና ሰዓት

የመዝጊያ ቀን

የመዝጊያ ሰዓት

የመክፈቻ ሰዓት

1

ሎት አንድ

የጥገና ዎርክ ሾፕ መሣሪያዎች ግዥ

200

100 ሺህ

ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም

4:00

4:30

2

ሎት ሁለት

የተለያዩ መኪናዎች እቃዎች ግዥ

200

100 ሺህ

ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም

8:00

8:30

 

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከላይ በሠንጠረዥ ውስጥ በዝርዝር እንድተገለፀው እና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካል መስፈርት መሰረት ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1.     በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፣ ቲን ቫት፣ በGP/PPA የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባችሁ እንዲሁም ከገቢዎች ሚ/ር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አ.ማ አጠገብ የቀድሞው እርሻ መሣሪያዎችና ቴክኒክ አገልግሎት አ.ማ. ግቢ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከላይ በእያንዳንዱ ሎት በተገለፀው ብር መሰረት በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

2.     ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ በግልጽ የሚታይና ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን ይኖርበታል።

3.     ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና (ለ60 ቀናት የሚቆይ) ማስከበሪያ ከላይ በተገለፀው መሰረት በሲ.ፒ.ኦ. ወይም በባንክ ጋራንቲ (unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ዋስትናው ለብቻው በአንድ ፖስታ ውስጥ ተደርጎ ከኦርጂናል ቴክኒካል ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል። የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የጸና ይሆናል።

4.     ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ዶክመንት መሰረት እያንዳንዱ ሎት-1 እና በሎት-2 ለየብቻ በማድረግ ቴክኒካል ኦርጂናልና ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሽያል በተለያዩ ፖስታ በማድረግ ፋይናንሽያል ሰነዱ ዋና እና ኮፒ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5.     ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት ከላይ በሠንጠረዥ ውስጥ በተገለፀው መሰረት ሆኖ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የቴክኒካል ጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል።

6.     ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

 

ስልክ ቁጥር:- +251911984467/+251913217657

 

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

 

Save Tender