በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ እቃዎች ማለትም ሲሚንቶ አሸዋ፣ ቆርቆሮ፣ ሚስማር የመሳሰሉትን ግዥ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች /ፈርኒቸር/ ግዥ፣ ለሞ/ወ/ወ/ስፖርት ጽ/ቤት በስፖርት ም/ቤት በጀት የስፖርት ቁሳቁስና ትጥቆች ግዥ፣ ለሞ/ወ/ወ/ውሃ ጽ/ቤት በተለያዩ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ እቃዎች ማለትም ሲሚንቶ አሸዋ፣ ቆርቆሮ፣ ሚስማር የመሳሰሉትን ግዥ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች /ፈርኒቸር/ ግዥ፣ ለሞ/ወ/ወ/ስፖርት ጽ/ቤት በስፖርት ም/ቤት በጀት የስፖርት ቁሳቁስና ትጥቆች ግዥ፣ ለሞ/ወ/ወ/ውሃ ጽ/ቤት በተለያዩ ቀበሌዎች ለሚያስገነባው የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታዎች በሙሉ ዋጋ ለማሰራት፣ ለሞ/ወ/ ወ/ግብርና ጽ/ቤት አይሰራውም መስኖ አውታር ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
2. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የማረጋገጫ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነዱን ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ማግኘት ይቻላል፣
4. ሚገዙትን እቃዎች እና የሚገነቡትን የግንባታ ዓይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለኤሌክትሮኒከስ እቃዎች ግዥ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር፣ ለቢሮ መገልገያ እቃዎች/ፈርኒቸር/ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ለስፖርት ቁሳቁስና ትጥቆች ግዥ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ለሁሉም ግንባታዎች የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ መሂ ማስያዝ አለባቸው፣
6. ለመስኖ ጥግና ግንባታ በዘርፉ የታደሰ ደረጃ 7 እና በላይ የብቃት ማረጋገጫ፣ ለመጠጥ ውሃ ግንባታዎች በዘርፉ የታደሰ ደረጃ 8 እና በላይ የብታት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታዉ በዚሁ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ የንፁህ መጠጥ ዉሃ ግንባታዎች፣ የአይሰራውም መስኖ አዉታር ጥገና ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ21ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታዉ በዚሁ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል ሁሉም ጨረታዎች ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡
8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር on6250146 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
10. የጨረታ መዝጊያዉ ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰአት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
አድራሻ፡- አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደ/ብርሃን 72 ኪሎ ሜትር ወደ ደሴ መስመር ከሚወስደው መንገድ ጣርማበር (ዋሻ) ወደ ምዕራብ 22 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
